Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በመገናኛ አካባቢ የተገነባው ስማርት የተሽከርካሪ ማቆሚያ የሙከራ ሥራ ጀመረ

0 1,319

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአዲስ አበባ ከተማ መገናኛ አካባቢ የተገነባውና በአንድ ጊዜ 90 ተሽከርካሪዎች የማስተናገድ አቅም ያለው ‘ስማርት የተሽከርካሪ ማቆሚያ’ የሙከራ ሥራ ጀመረ።

በተጨማሪም 50 ተሽከርካሪዎችን የመያዝ አቅም ያለው ‘የመሬት ላይ ተሽከርካሪ ማቆሚያ’ም አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

የከተማዋ የትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንደገለጸው፤ አዲሱ ዘመናዊ የተሸከርካሪ ማቆሚያ 15 ደረጃዎች አሉት።

መንግሥት በመደበው ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባው የተሽከርካሪ ማቆሚያ በጥቂት ቀናት ውስጥ የሙከራ ሥራውን አጠናቆ ወደ ሙሉ አገልግሎት እንደሚገባ ነው የተመለከተው።

በጽህፈት ቤቱ የመሠረተ ልማት ክፍል ተወካይ አቶ ትንሳኤ ወልደገብርኤል እንደገለጹት፤ የተሽከርካሪዎቹ ማቆሚያዎች በአካባቢው የሚታየውን የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅ ያቃልላሉ ተብሎ ይታመናል።

የተሽከርካሪ ማቆሚያው በ170 ካሬ ሜትር መሬት ላይ ያረፈ ነው።

ፕሮጀክቱ የሙከራ ሥራውን አጠናቆ ወደ ሙሉ አገልግሎት ሲገባ መንግሥት በተመነው ተመጣጣኝ ክፍያ አገልግሎት ይሰጣል።

ከ20 ለማያንሱ ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል እንደሚፈጥርም አቶ ትንሳኤ አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅት ቅድሚያ በተሰጣቸው በአንዋር መስጊድ፣ በቸርችል ጎዳና እና በወሎ ሰፈር አካባቢዎች የመሬትና ስማርት የተሽከርካሪ ማቆሚያ ግንባታ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በቀጣይም በመዲናዋ በተመረጡ 60 ቦታዎች የተሽከርካሪ ማቆሚያ ግንባታ ይከናወናል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy