NEWS

በቆሼ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች መኖሪያ ቤት ተሰጣቸው

By Admin

April 01, 2017

በቆሼ በደረሰው የአፈር መደርመስ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውና ኃብትና ንብረታቸውን ላጡ ወገኖች የመኖሪያ ቤት ተበረከተላቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች በንፋስ ስልክ ላፍቶና ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተሞች ውሰጥ በ24 ሚሊዮን ብር ወጪ የተሰሩ 110 የመኖሪያ ቤቶች ለተጎጂዎች አስርክቧል።

የከተማዋ ከንቲባ ዲሪባ ኩማ የቤቱን ቁልፍ ለተጎጂዎች ባስረከቡበት ወቅት እንዳሉት “የከተማ አሰተዳደሩ በተቻለ አቅም ተጎጂዎቹን የመርዳትና የማቋቋም ስራው ይቀጥላል” ብለዋል።

ቤቶቹ የተገነቡት ለኑሮ ተስማሚ በሆኑ አካባቢዎች በመሆኑ ተጎጂዎች ከህዝቡ ድጋፍ በተጎዳኝ ጠንክሮ በመስራት ኑሯቸውን ማሻሻል አለባቸው ነው ያሉት።

በቆሼ በደረሳው አደጋ ኮልፌ ቃራኒዮ ክፍለ ከተማ አስኮ አዲስ ሰፈር አካባቢ በ16 ሚሊዮን ብር የተገነቡ ቤቶች ለተጎጂ ቤተሰቦች ተብርክተዋል።

በሌላ በኩልም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍል ከተማ በ8 ሚሊዮን ብር ወጭ የተገነቡ ቤቶች ለተጎጂዎቹ የተሰጠ ሲሆን ቤቶቹ የውሃ፣የኤሌክትሪክ፣የመጸዳጃና የምግብ ማብሰያ መሰረተ ልማት የተሟላላቸው መሆኑ በርክክብ ወቅት ተገልጿል።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ነዋሪዎችም ህዝብና መንግስት ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አርቅበዋል።

በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻች እስካሁን በተካሄደው የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ 60 ሚሊዬን 998 ሺህ ብር በጥሬ ብር እና ከስድስት ሚሊየን ብር በላይ በዓይነት ድጋፍ ተሰብስቧል።