NEWS

በአልጄሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከፈተ

By Admin

April 14, 2017

የአልጄሪያው የውጭ ጉዳይና ዓለም ዓቀፍ ትብብር ሚኒስትር ራመታነ ላማምራና የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በአልጀርስ የኢትዮጵያን ኤምባሲ  በይፋ መርቀው ከፍዋል፡፡

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ በአልጄሪያ የሚገኙ ዲፕሎማቶችና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡

በዚሁ ጊዜ የአልጄሪያው የውጪ ጉዳይና ዓለም ዓቀፍ ትብብር ሚኒስትሩ ራምታነ ላማምራ እንደተናገሩት  ኢትዮጵያ ኤምባሲዋን በሀገሪቱ ኤምባሲ ባትከፍትም የሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ግን ጠንካራና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡

ለዚህ ደግሞ አልጀሪያ ከ40 አመታት ቀደም ብላ የዲፕሎማሲ ተወካይዋን በአዲስ አበባ  ማስቀመጧ የጎላ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የተለየ መሆኑን ያብራሩት ሚኒስትሩ በአፍሪካ ውስጥ የልማት አንቀሳቃሽ ሞተሮች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ሀገሪቱ ኤምባሲዋን መክፈቷ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ሚኒስትሩ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው ሀገራቸው ኤምባሲዋን በአልጀሪያ መክፈቷ የነበረውን የሁለቱን ሀገራት ዘላቂና ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ይበልጥ  ያጎለብተዋል ማለታቸውን የአልጄሪያ ፕረስ አገልግሎት አስነብቧል፡፡