NEWS

በኢትዮጵያ 10 በመቶ ህዝብ ለድብርት በሽታ ተጋላጭ መሆኑን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ ።

By Admin

April 09, 2017

በኢትዮጵያ 10 በመቶ ህዝብ ለድብርት በሽታ ተጋላጭ መሆኑን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ ።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በየዓመቱ መጋቢት 29 የሚከበረውን የዓለም የጤና ቀን “ ስለ ድብርት እንነጋጋር ” በሚል መሪ ቃል የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተከብሯል ።

የዓለም የአዕምሮ ጤና ችግር አካል የሆነው ድብርት በዓለም 300 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብን ለጉዳት እየዳረገ  ሲሆን፤በኢትዮጵያ ደግሞ 10 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ለድብርት በሽታ ተጋላጭ መሆኑ ሚኒስቴሩ ያወጣው መረጃ  ያመለክታል ።

የአዕምሮ ጤና ችግር በየትኛውም የህብረተሰብ ክፍል ላይ የሚከሰትና ዋና ዋና መንስኤዎችም ማህበራዊ  ቀውሶች ፤ ድንገተኛ ህመምና የተለያዩ ሱሶች  መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ጠቁማል ።

በአዕምሮ ጤና ላይ የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ  የአዕምሮ  ህሙማን  ቁጥር እያደገ በመምጣቱ የሚመለከታቸው አካላት  ትኩረት  ሰጥተው መሥራት እንደሚገባቸው ተመልክቷል ።

መንግሥት  ለአዕምሮ የጤና ችግር  አስፈላጊውን  የህክምና አገልግሎት በተገቢው መልኩ  ለመሥጠት ከአማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል  በተጨማሪ በኮተቤ  ሁለተኛው የአዕምሮ ሆስፒታል ተከፍቷል ።