በአገሪቱ ህገ ወጥ እንደሆነ የተደነገገለትን በሌሊት የሚሠጥ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን ህጋዊ የሚያደርግ ፖሊሲ እያዘጋጀ መሆኑን የፌደራል የትራንስፖርት ባለሥልጣን አስታወቀ ።
እንደ ባለሥልጣኑ ገለጻ በሌሊት ወቅት በህዝብ ትራንስፖርት አማካኝነት ለዓመታት ሲካሄዱ የቆዩት ጉዞዎች ቀደም ብሎ በወጡት አዋጆች ህገ ወጥ መሆኑን ተደንግጓል ።
ባለሥልጣኑ በህዝብ ትራንስፖርት አማካኝነት በሌሊት የሚሠጥ ህገ ወጥ የትራንስፖርት አገልግሎትን ለመከላከል እርምጃዎችን በመውሰድና የተለያዩ አሠራሮችን ለመዘርጋት ቢሞክርም ችግሩን ለማስወገድ አልቻለም ።
በአዲስ አበባ ከተማ ዋልታ ቴሌቪዥን ያነጋገራቸው የሌሊት ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች እንደሚናገሩት በአገሪቱ የመሠረተ ልማቶችና አሠራሮች በአግባቡ ከተዘረጉ የሌሊት ጉዞን ህጋዊ ማድረግ ይቻላል ብለዋል ።
የፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የሌሊት ትራንስፖርት አገልግሎትን ህጋዊ የሚያደርግ ፖሊሲን እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል