Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ቴዲ አፍሮ ግን

2 4,943

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ቴዲ አፍሮ ግን ፣ ነገስታቱን እና ባለሟሎቻቸውን ከሚያሞካሽበት ሰዓት እና ጊዜያቱ ላይ ትንሽ ቀንሶ ለአብዛኛው እና ዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል ወገናዊነቱን የሚገልጽበት ጊዜ ቢኖረው ምን ይለዋል?
አዎ ፣ በቀደሙት ዘመናት የተሰሩ ጥቂት መልካም ታሪኮች ነበሩን። ሆኖም ግን ፣ ባለብዙ ብሄር ፣ ብሄረሰብ ፣ ሃይማኖቶች ፣ ቋንቋዎች ፣ ባህሎች እና የመሳሰሉ እሴቶች በእኩልነት የማይስተናገዱባት የነበረችው ኢትዮዽያ ለአብዛኛው ህዝብ የፍዳ እና የማይመች ህይወት መግፊያ ሆና መኖሯን ሳይሰማ የቀረ አይመስለኝም። ይሄንንም ስል ፣ በራሱ ሞያ አካባቢ የነበሩትን ብርቅዬ የኪነጥበብ ሰዎችን እና ታላላቅ አትሌቶችንም ህይወት ጨምሮ ፣ ከእጅ ወደ አፍ ኖሮ ደሃ ሆኖ መሞት በጣም የተለመደ እንደነበርም በማሰብ ነው።
የኪነጥበብ ሰው ሆኖ የናጠጠ ሃብታም መሆን (እንዲህ እንደዛሬው) የማይታሰብበት ዘመናት ነበሩን። ጥላሁን ገሰሰ የሚባል በርካታ ትውልድ ያደነቀው እና ያከበረው ድምጻዊ ወይም መንግስቱ ወርቁ የሚባል የኳስ ንጉስ/ጠቢብ ወይም አበበ ቢቂላ የሚባል በዓለም የገነነ ስም ይዞ የረባ ኑሮ አለመኖር የሚቻልባት ሃገር ነበረችን። አንደነገሩ የሆነ ድርቅ ተከሰተ ማለትም ፣ በሚሊዮን ካልሆነ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ህይወት እንደቅጠል የሚረግፉባቸው ዘመናትም ነበሩ ፣ የቴዲን ቀልብ ሰቅዘው የያዙት የቀደሙ መሪዎች ዘመናት።
 እንዲሁ መሰረት በሌለው መንገድ እራስን/ሃገርን መካብ እና በከንቱ በመመጻደቅ እውነቱን መቀየር አይቻልም። ችግሩን ማመን እና ለመፍትሄመንቀሳቀሱ የተሻለ ውጤት ይኖረዋል ፤ ባለፉት 25 ዓመታት ገደማ እንዳየንው።
ሰሞኑን ያወጣው ሙዚቃ ላይም እንዲሁ በዘልማድ የሚባል እና አንዳች እውነት የሌለውን አባባል ተጠቅሟል።
     የኢትዮዽያ ባንዲራ እንዴት ሆኖ ሰማይ ላይ እንደታየ አልገባኝም። አንድ አንዶች ፣ ቀስተዳመናን አረንጓዴ ፣ ቢጫ እና ቀይ የኢትዮዽያ ባንዲራ ቀለም ነው ያለው በማለት የሚያወሩትን አፈ-ታሪክ ይዞ ከሆነ በጣም ተሳስቷል። ቀስተ-ደመና ሰባት ዓይነት ቀለማትን የያዘ እና በዚህ ዘመን ደግሞ ግብረሰዶማውያን እንደ መለያቸው የሚታወቁበት ነው። ለነገሩ ፣ እግዜርም ቀስተደመናን የፈጠረው ከኢትዮዽያ ባንዲራ ቀለም አይቶ ነው ማለትም ይቻል ይሆናል ፣ ምንም ቢባል “ለምን?” ብለው የማይጠይቁ ሰዎች በመኖራቸው።
     ለማንኛዉም ፣ ከብዙ ወሬ/እንጉርጉሮ ጥቂት በተግባር የተገለጸ የሃገር ፍቅር ይበልጣል። ከበርካታ የህብረተሰብ ክፍል ጋር እልህ መጋባትም የሚያዋጣ አይመስለኝም እና ትንሽ ረጋ ቢል ይጠቅመዋል እላለሁ።
begashaw kebede
  1. Getaneh says

    የኢትዮጵያን እድገት ከሚስብክና ከሚመኝ ዜጋ የማይጠበቅ ተራ ወሬ፡፡ Just accept the fact that Teddy did an amazing job and almost everyone is loving it.

    እኔ የምለው:
    ላለፈው 20 አመት ኮንዶ ተሰራልን
    ህንፃችን በዛ ኢትዮጵያ ኑሪልን…

    ምናምን አይነት ግጥም ያለው ዘፈን ካልቴዘመ በቃ…

  2. ethiopia yegnanat says

    ይህንን አንተና ደንቆሮ የወያኔ ቡችሎች አላችሁ፡፡ ኤደልም ኢትዮጵያ መላው አለም ደግሞ ቴዲን ከአንተ በተቃራኒ በፍቅር ያዋል፡፡ እንደ አንተ በቂጡ የሚያስብ ጥቂት ግን እንደ አንተ የሚያስብ ደንቆሮ ኤጠፋምና ይሄንን ማለትህ ምነቡም አይደንቅም፡፡ እኔ ከሞትኩ አይነት ነህና…….. እንደ አንተ በቂጣቸው የሚያስቡ ጥቂት ጥርቅሞች ሳይሆኑ በጭንቅላታቸው የሚያስቡ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ስለ ተወዳጁና ብርቅየው አርቲስት ቴዲ አፍሮ ምን እንዳሉ ጎግል ላይ ገብተህ አንብበህ ለመረዳት ሞክር አንተ ባንዳ ሀገር ሻች ልጅ የአባትህ ለገሰ ቢቴ፡፡ ስለዚያ ገንጣና ቫምፓየር ለገሰ ዜናዊማ ምን ብሎ ዘፍናል……..፡፡ እያንዳንዳችን በስራችን ልክ ነው የምንታወሰው፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy