English

አለም አቀፉ የፈጣን ምግቦች አምራች ኩባንያ ያም በኢትዮጵያ 10 ቅርንጫፎች ሊከፍት ነው

By Admin

April 26, 2017

የዩናይትድ ስቴትስ ግዙፉ ያም ብራንድስ አለም አቀፍ ኩባንያ እና የኢትዮጵያው በላይ አብ ፉድስ እና ፍራንቻይዝ ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ በኢትዮጵያ 10 የፒዛ ምግቦች የሚሸጡባቸው ሬስቶራንቶች ለመክፈት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የመጀመሪዎቹ ሶስቱ በስድስት ወራት ስራ የሚጀምሩ መሆናቸውን እና በሶስት አመታት ጊዜ ውስጥ 10 የፒዛ ቤቶች እንደሚከፈቱ የፕሮጀክቱ ባለአክስዮን ሚካኤል ገብሩ ለሬውተርስ ተናግረዋል።

መቀመጫውን ኬንታኪ ያደረገው ያም በአፍሪካ ከ1 ሺህ በላይ የፒዛ ምግቦች ሬስቶራንቶች ደረጃውን ጠብቀው በመለያው የሚሸጡ ሲሆን፥ ኩባንያው በአህጉሪቱ 188 ፍቃድ ያላቸው ቅርንጫፎች እንዳሉት ተዘግቧል፡፡

ያም ብራንድስ በአሜሪካ እና በመላው አለም ፈጣን ምግቦችን በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን፥ 42 ሺህ 692 ሬስቶራንቶች የፈጣን ምግብ ምርቶችን በኩባንያው ደረጃ እና መለያ የሚሸጡ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ከተጠቀሰው ቁጥር ውስጥ 8 ሺህ 927 የሚሆኑት በኩባንያው በቀጥታ በባለቤትነት የሚተዳደሩ ናቸው።

ምንጭ፦ ሬውተርስ