አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአየርላንድ ፕሬዚዳንት ሚስተር ማይክል ሂግንስ አቀረቡ።
አምባሳደር ሬድዋን የኢትዮጵያና አየርላንድን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል።
የአየርላንዱ ፕሬዝዳንት ሚስተር ማይክል ሂግንስ በበኩላቸው አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ወዳጅነትና አጋርነት አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገሮች የሚመጡ ስደተኞችን በማስተናገድ እያከናወነች ያለችውን ተግባርም አድንቀዋል።
ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት አገሪቷ እያስመዘገበች ያለችውን ፈጣን ዕድገት መረዳታቸውን ገልጸዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መግለጫ አመልክቷል።
ኢትዮጵያና አየርላንድ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1994 ነው።