አፍሪካዉያን የተፈጥሮ ሃብታችንን በአግባቡ የማንጠቀም ከሆነ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ጠ/ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ፡፡
በ6ተኛው ሰላምና ደህንነት ላይ ትኩረቱን አድርጎ በባህር ዳር እየመከረ ባለው የጣና ፎረም የተገኙት ጠ/ሚንስትሩ አፍሪካ የተፈጥሮ ሃብቷን በአግባቡ መንከባከብ እንደሚገባትና በአህጉሪቱ የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ማደግ እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡
የጣና ፎረም ሊቀመንበርና የቀድሞ የናይጄርያ ፕሬዝዳን የነበሩት አሊሴጎን ኦባሳንጆ በበኩላቸው አፍሪካ ቴክኖሎጂና የቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን በመጠቀም ዕድገቷን ማፋጠንና የቴክኖሎጂ መሰረት መጣል እንደሚገባት ነው የገለጹት፡፡
አፍሪካ ልጆቿን በማስተማር ዕድገቷን ማፋጠን አለባት ያሉት ደግሞ የጣና ፎረም ምክትል ሊቀመንበር ቶማስ ኬኖቴ ናቸው፡፡
አፍሪካ ሀብቷን በአግባቡ ለመጠቀም ጥራት ያለው ትምህርት ላይ ትኩረት አድርጋ መስራት እንደሚገባት ተናግረዋል ምክትል ሊቀመንበሩ፡፡
ዘ ስቴት ፍ ፒስ ኤንድ ሴኩሪቲ በሚል ርዕስ እየተካሄደ ያለው 6ተኛው የጣና ፎረም በቡድንና የሁለትዮች ውይይት እንደምቀጥል ተገልጿል፡፡
ፎረሙ የሚካሄድበት የአማራ ክልል የእራት ግብዣ ፕሮግራም መዘጋጁት ከስፍራው የተኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በአዝመራው ሙሴ