Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ከአፍሪካ ሀገራት ጠንካራ ድጋፍ እንዳላቸው ኒውስ ታይም ይዞት የወጣው ዘገባ ያስረዳል፡፡

0 1,370

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም የአለም ጤና ድርጅትን ለመምራት በሚያደርጉት ሂደት ከአፍሪካ ሀገራት ሙሉ ድጋፍ እያገኙ መሆናቸውን ዘኒውስ ታይምስ አስነበበ

ሚያዝያ 04/2009 ዓ.ም በሚቀጥለው ግንቦት የአለም ጤና ድርጅት ጉባኤ በስዊትዘርላንድ፤ ጄኔቫ ሲካሄድ 194 አባል ሀገራት በድምፃቸው አዲሱን የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ይመርጣሉ፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ከአፍሪካ ሀገራት ጠንካራ ድጋፍ እንዳላቸው ኒውስ ታይም ይዞት የወጣው ዘገባ ያስረዳል፡፡

የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የመንግስት ቃል አቀባይ ሉሲ ሙሺኪዋቦ አለም አቀፉን ትልቅ ድርጅት የመምራት አቅም ያላቸው ዶ/ር ቴድሮስ መሆናቸውን ለኒው ታይምስ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል፡፡

“ይህ የአለም ጤና ድርጅት ምርጫ ለአፍሪካ በጣም አስፈላጊ ነው ፤እንደ አህጉር ምርጥ ብቃት ያላቸው እጩ አሉን እሳቸውም ዶ/ር ቴድሮስ ናቸው“ ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ አያይዘውም ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ከዶ/ር ቴድሮስ ጎን መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

በዩጋንዳ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ጉዳይ ሚኒስትር ጁሊየስ ማጋንዳ በበኩላቸው የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሸናፊ በመሆን 8ኛው ዳይሬክተር ጀነራል ለመሆን ብቁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በአባል ሀገራት የተመረጡ እጩዎች ማንነት እኤአ መስከረም 23 ቀን ይፋ ከተደረገ በኋላ የአለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ቦርድ ለቀጣይ ውድድር የሚዘጋጁ አምስት እጩዎችን ዝርዝር ጥር 01 /2017 አውጥቷል፡፡

እነሱም ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም፤ዶ/ር ሳንያ ኒሸር ከፓኪስታን፤ዶ/ር ዴቪድ ናቫሮ ከዩናይትድ ኪንግደም፤ፕሮፌሰር ፊሊፔ ዱስቴ ብላዚ ከፈረንሳይ እና ዶ/ር ፍላቪያ ቡስትሪዮ ከጣሊያን ናቸው፡፡

ከእነዚህ መካከል ሶስቱ እጩዎች ዶ/ር ቴድሮስ፤ ዶ/ር ናባሮ እና ዶ/ር ኒሽታር ብቻ ነበሩ ለመጨረሻው ዙር ምርጫ የተሸጋገሩት፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ምርጫውን ካሸነፉ በአለም ጤና ድርጅት የ69 አመታት ታሪክ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ እና አፍሪካዊ መሪ ይሆናሉ፡፡

እኤአ ግንቦት 23 ቀን በሚካሄደው ምርጫ ያሸነፈ ተወዳዳሪ ከወቅቱ ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ማርጋሬት ቻን ስልጣን ተረክቦ ሀምሌ 01/2017 ስራውን በይፋ ይጀምራል፡፡

ምንጭ፡ዘኒውታይምስ.ኮም

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy