Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች—ሚኒስትር ዋርተን

0 295

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አለም በቀውስ እየተናጠች ብትሆንም እንግሊዝ ኢትዮጵያን መደገፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል የአገሪቱ የአለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ጄምስ ዋርተን መናገራቸውን የተቋሙ ድረ ገፅ አስነብቧል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፈው አመት የገጠማትን የድርቅ አደጋ ተከትሎ ሚኒስትሩ በወቅቱ የትግራይ ክልልን መጎብኘታቸውን ድረ ገፁ አስታውሶ የተቋማቸው እገዛ ኤሊኒኖ ያስከተለውን የድርቅ ጉዳት ለመከላከል ማገዙን አስነብቧል፡፡

እንግሊዝ በዚህ አመት መጀመሪያ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ በመጨመር 800 ሺ የሚጠጉ ዜጎች ንፁህ ውሃ እና ምግብ እንዲያገኙ የምግብ  እጥረት የገጠማቸው ህፃናት ደግሞ አስቸኳይ የተመጣጠነ ምግብ እንዲደርሳቸው ማገዟንም ዘጋቢው ፅፏል፡፡

ኢትዮጵያ 800 ሺ የሚጠጉ ስደተኞችን በማስተናገድ ከአለም አገራት ቀዳሚውን ተርታ የያዘች ሲሆን ሚኒስትሩ በቆይታቸው በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኘውን የእንዳባጉና የስደተኞች መጠለያ መጎብኘታቸው ተገልጿል፡፡

በጎረቤት አገራት ያለውን ሰብአዊ ቀውስ ተከትሎ ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ኤርትራ ብዛት ያላቸው ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆኑ ይታወቃል፡፡

“በድርቁ ምክንያትና በጎረቤት አገራት ባለው ቀውስ የተነሳ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በከፋ ሁኔታ ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡እንግሊዝ እያደረገች ያለውን ድጋፍ በአካል ተገኝቼ ለመመልከት ችያለሁ፡፡ እገዛችን ለውጥ እያስገኘ ነው፡፡“

“በተመሳሳይ የአገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲያድግና የግሉ የንግድ ዘርፍ የስራ እድል እንዲፈጥር ድጋፋችንን እንቀጥላለን፡፡የኢትዮጵያና የእንግሊዝን ግንኙነት የሚያስጠብቁ ቀጣይነት ያላቸውን እገዛዎችም እናበረክታለን” ብለዋል ፡፡

በአዲስ አበባ የከተመውንና  ከእንግሊዝ የልማት ድርጅት ድጋፍ ያገኘውን የእንግሊዛውያን የቆዳ ማምረቻ ፋብሪካ የጎበኙት ሚኒስትሩ ከሰራተኞቹ ጋር መነጋገራቸው ተገልጿል፡፡

እንግሊዝ በረጅም ጊዜ እቅድ የምታደርገው ድጋፍ ድህነትን ለመቀነስ የራሱን አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን መመልከታቸውንም ጀምስ ዋርተን ተናግረዋል፡፡በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ኢትዮጵያን የጎበኙት የአለም አቀፍ ልማት ፀሐፊዋ ፕሪቲ ፓቴል በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ  ዙሪያ ነዋሪ የሆኑ  60 ሺ ሰዎችን የስራ እድል ተጠቃሚ የሚያደርግ የኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጂ ይፋ ማድረጋቸውንም አስታውሰዋል፡፡

እንግሊዝ ባለፉት አምስት አመታት ያደረገችው ድጋፍ 11 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያኖችን ተጠቃሚ ማድረጉን ጠቅሶ ድረ ገፁ ዘገባውን ደምድሟል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy