Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከሦሥት አንዱ ተማሪ የሆነባት አገር – ኢትዮጵያ

1 833

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከሦሥት አንዱ ተማሪ የሆነባት አገር – ኢትዮጵያ

አባ መላኩ

በአገራችን ባለፉት  ሃያ ስድስት ዓመታት በፖለቲካው፣ ኢኮኖሚው እና ማህበራዊ መስኮች ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል። በመመዝገብ ላይ ናቸው። በፖለቲካው መስክ አገራችን ህገ-መንግስታዊ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት መስርታ ሁላችንንም እኩል አድርጋናለች። የህዝቦች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተረጋግጠዋል።

ዛሬ ኢትዮጵያዊነት በፍላጎት እንጂ በሃይል በህዝቦች ላይ የሚጫን  ዜግነት  ሳይሆን  ትግራይ ሆኖ ኢትዮጵያዊ፣ አማራ ሆኖ ኢትዮጵያዊ፣  ኦሮሞ ሆኖ ኢትዮጵያዊ፣  ሶማሌ ሆኖ ኢትዮጵያዊ፣ ወዘተ   የሆነ የቡድን ማንነትና ብሄራዊ ማንነት የተቆራኙባት አገር ለመሆን በቅታለች። በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ሁሉም ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች  ፈቅደውና ወደው ኢትዮጰያዊ ዜግነትን የተጎናጸፉባት  አገር ሆናለች።  አዲሲቷ ኢትዮጵያ ብዘሃነትን የተቀበለች የዜጎቿን ማንነት ማክበር የቻለች በመሆኗ ዘላቂ ሰላምና ልማትን አረጋግጣለች።

አገራችን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ በመቻሏ በኢኮኖሚው መስክ ባለፉት 15 ዓመታት  ተከታታይና ባለሁለት አሃዝ ፈጣን እድገት በሁሉም መስክ  በማስመዝገብ  ላይ ትገኛለች። ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ካለችው  የኢኮኖሚ ዕድገት ዜጎች ፍተሃዊ ተጠቃሚ መሆናቸውን ከእነሱ ምስክርነት ባሻገር  ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ያወጧቸው ሪፖርቶች ይህንኑ አረጋግጠዋል።

ከ20 ዓመት በፊት አጠቃላይ አገራዊ ምርት 12 ቢላዮን የአሜርካ ዶላር ገደማ የነበረ ሲሆን  ይህ አሃዝ አሁን ላይ ወደ 72 ቢሊዮን ዶላር ገደማ አድጓል።  በተመሳሳይ በዚያን ወቅት  የአንድ ኢትየጵያዊ ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ 250 ዶላር የነበረው አሁን ላይ ወደ 800 ዶላር አካባቢ ማደረስ ተችሏል።  በተመሳሳይ በዚያን ወቅት  በአገራችን በከፋ የድህነት ወለል  ይኖር የነበረው ዜጋ ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛት  44 በመቶ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ይህን በግማሽ መቀነስ ተችሏል። እነዚህን እውነታዎች ማንም ሊያስተባበላቸው የማይቻለው ሃቅ ናቸው። እውነቱን እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ይነስም ይብዛም  ዕድገቱ በእያንዳንዳችን ቤት ለውጥ አምጥቶልናል።

ልማትን ለማፋጠን፣ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት እና ሠላም ለማስፈን ትምህርት መሠረታዊና ቁልፍ መሣሪያ መሆኑን የመንግስት እምነት በመሆኑ ለዘርፉ መስፋፋት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶታል።  የማህበራዊ ዘርፍ ልማት የፍተሃዊ የሃብት ክፍፍል ማሳያ ተደርገው ከሚወሰዱ ነገሮች መካከል አንዱ መስፈርት ነው።  በመሆኑም ባለፉት ሁለት ዓስርት ዓመታት  አገራችን ከኢኮኖሚ ዕድገቱ ጎን ለጎን የማህበራዊ መገልገያዎችን በማስፋፋት ረገድ ውጤታማ  ነበረች ማለት ይቻላል።

አሁን ላይ በትምህርት ማስፋፋት ረገድ ኢትዮጵያ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር ወደ 30 ሚሊዮን ይጠጋሉ። ይህ ቁጥር የበርካታ አፍሪካ አገሮችን የህዝብ ቁጥር ይበልጣል። ይህን ቁጥር ዛሬ ላይ በአገራችን በመንግስት ወጪ በትምህርት ላይ የሚገኝ መሆኑ ሲታይ መንግስት ለትምህርት ዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ያሳያል። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ተደራሽነት በአገራችን ሙሉ ለሙሉ በሚያሰኝ ደረጃ ማድረስ እየተቻለ ነው።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት በድርግ  መንግስት ማብቂያ ላይ  በአገራችን 4 ሺህ የሚሆኑ የመጀመሪያ ደረጃና 278 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ 16 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛዎች እንዲሁም ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች  ብቻ ነበሩ።  አጠቃላይ የተማሪዎች ቁጥርም ከ2 ሚሊዮን ያልበለጡ ነበሩ። ይህ አሃዝ ከወቅቱ የአገሪቱ የህዝብ ቁጥር ጋር ሲሰላ በዓለም ላይ ዝቅተኛ የትምህርት ተሳትፎ አላቸው ከሚባሉ አገሮች ተርታ የሚያስመድብ  ነበር። በስርጭት ረገድም በከተሞችና ዙሪያቸው ከመገደቡ ባሻገር ከፆታም አኳያ ሚዛናዊነት የጎደለው ነበር። በተለይ  በአርሶና አርብቶ አደሮች አካባቢ ተሳትፎው ከሌሎች አካባቢዎች እጅግ ይከፋ ነበር።

የኢፌዴሪ መንግስት ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ለማህበራዊ ልማት ዘርፍ መስፋፋት በሰጠው ትኩረት  በአሁኑ ወቅት የአንደኛ ደረጃ የትምህርት ተቋማት ቁጥር ከ39 ሺህ በላይ እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት 3,350 በላይ የደረሰ ሲሆን የተማሪዎችም ቁጥር ወደ 30 ሚሊዮን  ማድረስ ተችሏል። ይህ ቁጥር ከሶስት ኢትዮጵያዊ አንዱ ተማሪ እንደሆነ ያሳያል። ይህን ሃይል በአግባቡ ማስተናገድ ከተቻለ ለነገዋ ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም ነው።

ዛሬ ላይ በትምህርት ማስፋፈት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ አገር ለመሆን በቅታለች።  የኢፌዴሪ መንግስት ሕጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማር መብታቸው እንዲከበር በማድረጉ በአገር አቀፍ ደረጃ በ51 ቋንቋዎች ትምህርት እየተሰጠባቸው ይገኛል። የአገራችን የመጀመሪያ ደረጃ አጠቃላይ የትምህርት ተሳትፎ ከ20 በመቶ በታች የነበረው አሁን ላይ ከ95 በመቶ በላይ ማድረስ ተችሏል። ይህም በዓለም ዓቀፍ መስፈርት ከፍተኛ  የሚያስብል ነው።

ለዩኒቨርስቲ ትምህርት ማዘጋጃ በሆነው የመሰናደ ትምህርት ፕሮግራም ብቻ በያዝነው ዓመት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን በመማር ላይ ናቸው። ሌላው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ነው። በአሁኑ ወቅት አገራችን ኢኮኖዋን ከግብርና  ወደ ኢንደስትሪ መር   ለማድረግ እየሰራች ባለችው መዋቅራዊ  ሽግግር በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ሀይል ከማቅረብ አኳያ የሙያና ቴክኒክ  ዘርፍ ያላቸው  አስተዋጽዖ እጅግ ወሳኝ ነው። በመሆኑም  ከሃያ ስድስት ዓመታት በፉት በጥቂት የከተማ አካባቢዎች ተወስኖ የነበሩት 16 ያህል ቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ዛሬ በየወረዳው 1,350 ተቋማት ማዳረስ ተችሎል።

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ስራ ፈጣሪ ዜጋ በማፍራት ረገድ ያላቸው አስተዋፅዖ ከፍተኛ ነው። በአሁኑ ወቅት በመካሄደ ላይ ባለው ከግብርና መር ወደ ኢንደስትሪ መርህ መዋቅራዊ የኢካኖሚ ሽግግር ውስጥ በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ሀይል ከማቅረብ አኳያ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ዘርፍ ዓለም አቀፊዊ ተሞክሮ ተቀምሮ ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ ስትራቴጂ በማውጣት ላይ ይገኛሉ።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ማስፋፋት በተመለከተም አገራችን ከፍተኛ ለውጥ ማሳየት ችላለች። በደርግ መንግስት ወድቀት ማግስት አገራችን የነበሯት ሁለት ዩኒቨርስቲዎች አሁን ላይ ወደ 36 አድገዋል። ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርታቸውን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ በመከታተል ላይ ናቸው።  ከእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች በተጨማሪ በሁለተኛው ዕደገትና ትራንስፍርሜሽን ዕቅድ አስራ አንድ አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎች በግንባታ ላይ ናቸው።

 

ሌላው ማንሳት የምፈልገው የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርትን ነው። ጎልማሳው በአገራችን ልማት እንቅስቃሴ ላይ ንቁና ወሳኝ ተሣትፎ እንዲያደርግ የተቀናጀ ተግባር ተኮር የትምህርትና ሥልጠና አሰጣጥ ገጠሩን በመቀየር ያለው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው። የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርትን አርሶና አርብቶ አደሩ በአገራችን ልማት ወሳኝ ተሳትፎ እንዲያደርግ አስችሎታል። ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለመሰለፍ የዜጎች የማንበብና የመጻፍ ምጣኔ 85% መደረስ ይኖርበታል። አሁን አገራችን ካለችበት 65% ጋር ሲነፃፀር ልዩነቱ ቀላል የማይባል ቢሆንም በተጀመረው ፍጥነት መጓዝ ከተቻለ ማሳካት አገራችን በጥቂት አመታት እንደምታሳካው ጥርጥር የለም። ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት አርሶና አርብቶ አደሩን በአካባቢ ጥበቃ፣ በአካባቢና የግል ንጽህና፣ ኮሙዩኒቱ ፖሊሲንግ፣ ስነተዋልዶ ወዘተ እንዲያውቁ በማገዙ አርሶና አርብቶ አደሩ በአገራችን ፈጣን ልማት ያለውን አስተዋጽዖ እንዲያድግ አስችሎታል።

ሌላው ለሁሉም ዜጋ ማለትም በፆታ፣  ልዩ ፍላጎት ባላቸው ህጻናትና ወጣቶች፣ ልዩ ደጋፍ በሚሹ ክልልችና የአርብቶ አደር አካባቢዎች ወዘተ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ መስራት በመቻሉ የትምህርት ዕድልን   ፍተሃዊ   ማደረግ  ተችሏል። በትምህርት ረገድ ይህን ውጤት ማስመዝገብ የተቻለው ግልጽ የሆኑ ፖላሲዎችና ስትራቴዎቻችን መንግስት ማዘጋጀትና  ተግባራዊ ማድረግ በመቻሉ ነው። ከዚህም ባሻገር መላው ህብረተሰብ ልጆቹን በአግባብ መግቦና አልብሶ እንዲሁም የትምህርት መሣሪያ አሟልቶ ከመላክ ጎን ለጎን ለትምህርት ዘርፉ  ስኬት በግልም በቡድን   ከመንግስት ጎን  በመሰለፉ ያበረከተው አስተዋጽዖ እጅግ ከፍተኛ ነው። በመሆኑም በቀጣይ ይህን መልካም ጅምር አጠናክሮ በመቀጠል ለተሻለ ወጤት መትጋት ተገቢ ነው።

 

  1. Eyob Gebre says

    still EPRDF compare itself with Derge after 25 years !! shame on you !! time, place and value are critical for comparison. please compete and compare yourself with other countries in Africa !!! i hate this kind of propaganda. I belived by EPRDF specially TPLF ……please change your leadership and organization. Viva Ethiopia

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy