Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከሰበታ በሬ ገዝተው ወደ አዲስ አበባ ሲያመሩ የነበረ ግለሰብ በገዙት በሬ ተወግተው ህይወታቸው አለፈ

0 1,903

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከሰበታ በሬ ገዝተው ወደ አዲስ አበባ ሲያመሩ የነበረ ግለሰብ በገዙት በሬ ተወግተው ህይወታቸው አልፏል።

በአደጋው ህይታቸውን ያጡት ግለሰብ አቶ ተጎዱ ጌታቸው ይባላሉ።

ነዋሪነታቻው በላፍቶ ክፍለ ከተማ የነበረው ግለሰብ በበኣሉ ዋዜማ ወደ ሰበታ አንቅተው የገዙትን በሬ በክፍት ተሽከርካሪ ጭነው ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ነው አደጋው የደረሰው።

አሳዛኙ አደጋ የተከሰተውም እንዲህ ነው፤ በአይሱዙ የተጫነው በሬ ከግብይት ስፍራው ተነስቶ ትንሽ ከተጓዘ በኋላ ሰበታ ከተማ 03 ቀበሌ ሲደርስ ከተሽከርካሪው ላይ ዘሎ ይወርዳል።

በሬውን የዘጉት ግለሰብም የበሬውን መውረድ ሲያዩ ከተሽከርካሪው በመውረድ በሬውንን ለመያዝ ከኋላው ይከተሉታል።

በዚህ አባሮሽ ላይ እያሉ በሬው ወደ ኋላ በመመለስ ካሳደዳቸው በኋላ አንገታቸው ሰር ይወጋቸዋል።

በውጊያው ክፉኛ የተጎዱት ግለሰብ ለህክምና ወደ አለርት ሆስፒታል ቢወሰዱም ህይወታቸው ሊተርፍ አልቻለም።

መረጃውን ያደረሰን የሰበታ ከተማ ፖሊሲ ጣቢያ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ምክትል ኮማንደር አደም ሀሰን ናቸው።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy