Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከሳዑዲ ዓረቢያ የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን የግል ንብረቶቻቸውን ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ ተፈቀደ

0 837

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የግል መገልገያ እቃዎቻቸውን ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ መፈቀዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት ተመላሾቹ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በሳዑዲ ዓረቢያ በኖሩበት ወቅት ያፈሯቸውን የግል መገልገያ ዕቃዎች ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ያስገባሉ ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡

መንግስት ሳዑዲ ዓረቢያ በሰጠችው የምህረት ጊዜ አዋጅ ኢትዮጵያውያን ተመላሾች የደከሙበትን ንብረት ይዘው እንዲመለሱ ለማበረታታት፥ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አመላክቷል።

ዜጎች ለዓመታት ይኖሩበት ከነበረው ሳዑዲ ዓረቢያ ተገደው ሲወጡ ይዘዋቸው የሚመጡት 21 ዓይነት የግል መገልገያ ዕቃዎችን ይዘው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እድል መፈጠሩም ተገልጿል።

በመሆኑም የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ የጋዝ ምድጃ፣ ቴሌቪዥን፣ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር እና የሌሎች እቃዎችን ዝርዝር በሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ እና በአካባቢው በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ማግኘት ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎች ወደ ሀገር እንዲመለሱ የጉዞ ሰነድ የሚሰጡ ተጨማሪ ማዕከላትንም አቋቁሟል፡፡

የጎዞ ሰነድ የሚሰጡ ሪያድ ሚሲዮን፣ ደማም፣ ቡረይዳ እና ዋዲ ደዋስር በጅዳ ቆንስላ ጽህፈት ቤት እና በአካባቢው በመካ ላይ፣ ኸሚስሽጥ፣ ጄዛን እና መዲና በተከፈቱ ማዕከላት ዝርዝር መረጃ ማግኘት እንደሚቻልም በመግለጫው ተጠቅሷል።

መግለጫው ተመላሾቹ ያለ ምንም እንግልት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አንድ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ከሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ጋር በትብብር እየተሰራ ይገኛል ብሏል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy