Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዘጠኝ ባንኮች በ11 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ግንባታ እያከናወኑ ነው

0 1,188

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ዘጠኝ የንግድ ባንኮች ከ11 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ግንባታ እያከናወኑ ነው።

የዳሽን ባንክ የዋና መስሪያ ቤት ህንጻን በአዲስ አበባ ሰንጋ ተራ አካባቢ ገንብቶ በማጠናቀቅ ላይ ነው።

በተጨማሪም በደሴና በአራት ኪሎ አካባቢ ቅርንጫፍ ግንባታ እያካሄደ ሲሆን በአጠቃላይ ለህንፃዎቹ ግንባታ 1 ነጥብ 08 ቢሊየን ብር ወጪ ማድረጉን የባንኩ የማርኬቲንግና ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ አለባቸው ተናግረዋል።

Dashen-Bank-Head-Office.jpg

ህብረት ባንክም በአዲስ አበባ ባለ 32 ፎቅ ህንፃ እያስገነባ ሲሆን ለግንባታው 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ እንደሚደረግበት ተገልጿል።

United-Bank-of-Addis-Ababa-Söhne-Partner-Architekten-and-Miot-BET-Architects-2.jpg

የወጋገን ባንክ የማርኬቲንግና የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ፍቅሩ ወልደትንሳኤ በበኩላቸው፥ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ ስታዲየም አካባቢ «ወጋገን ታወር» በሚል ስያሜ በ2 ሺህ 400 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ባለ 23 ፎቅ ህንፃ ሆኖ እየተገነባ መሆኑን ተናግረዋል። የግንባታ ወጪውም 800 ሚሊየን ብር መሆኑን ነው የገለጹት።

የአቢሲኒያ ባንክ ለገሃር አካባቢ በ350 ሚሊየን ብር ወጪ እያስገነባው ያለው ባለ 250 ክፍሎች መንታ ፎቅ ጊዜያዊ ዋና መስሪያ ቤት እየተጠናቀቀ ነው።

የባንኩ የማርኬቲንግና ኮሙዩኒኬሽን ኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ አስቻለው ታምሩ፥ በቋሚነት የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በመሆን የሚያገለግለውን ህንፃ ለመገንባትም ቦሌ ጨፌ ኦሮሚያ አካባቢ 4 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ በሊዝ መግዛታቸውን ገልፀዋል።

ሜክሲኮ ፌዴራል ፖሊስ አካባቢም 2 ሺህ 500 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፥ ለሁለቱ ቦታዎች የሊዝ ግዥ 110 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉን ተናግረዋል።

the_15_story_bld_bought_by_boa.jpg

የአንበሳ ባንክ በበኩሉ በመቀሌ ከተማ 2 ሺህ ካሬ ሜትር ወስዶ ባለ10 ፎቅ ህንፃ ለመገንባት እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል።

የአባይ ባንክ ደግሞም ደግሞ በአዲስ አበባ፣ ባህርዳርና ደሴ ለባንኩ የሚሆኑ የቢሮ ህንፃ ግንባታዎችን ለማካሄድ የግንባታ ጨረታ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል።

የባንኩ የቢዝነስ፣ ዲቨሎፕመንትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሌ አበራ እንዳሉት፥ በአዲስ አበባ ለዋና መስሪያ ቤት የሚገነባው ህንፃ 1 ሺህ 600 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን፥ ለግንባታው 800 ሚሊየን ብር ወጪ ይደረጋል።

የባህርዳሩ ህንፃ በ4 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ባለ10 ፎቆ ህንፃ የሚገነባ ሲሆን፥ ወጪውም ከ300 እስከ 500 ሚሊዮን ብር ይገመታል ነው ያሉት አቶ ኃይሌ።

ደሴ ላይም በ500 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ህንፃ ለመገንባት ዝግጅት እየተደረገ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፥ በቀጣይ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ለቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ግንባታ ለማካሄድ እቅድ ተይዟል ብለዋል።

የአዋሽ ባንክ በበኩሉ በዲዴሳ ባለሁለት ፎቅ፣ ጅማ ባለስድስት ፎቅ፣ ቢሾፍቱ ባለአራት ፎቅ እና በአዲስ አበባ ባለ11 ፎቅ የህንፃ ግንባታዎችን እያካሄደ ይገኛል።

የባንኩ የማርኬቲንግና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አንዱዓለም ኃይሉ፥ ከሰባት ዓመት በፊት ለዋናው መስሪያ ቤት ባለ18 እና ባለ16 ወለል መንታ ህንፃዎችን በ230 ሚሊየን ብር መገንባታቸውን አስታውሰዋል።

ባንኩ በተለያዩ ቦታዎች የ10 ህንፃዎችን ግንባታ አጠናቆ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንና በቀጣይም ግንባታ እንደሚያካሂድም ገልጸዋል።

CBE.jpg

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በምስራቅ አፍሪካ ግንባር ቀደም የሆነ ዘመናዊ ህንጻ እያከናወነ ሲሆን፥ ለግንባታውም 5 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በጀት መመደቡን የኢትዮጵያ ፕረሬስ ድርጅት ዘግቧል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy