የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኢትዮጵያ ከተለያዩ አገራት ጋር ያደረገቻቸውን የሁለትዮሽ ስምምነቶች ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።የሁለትዮሽ ስምምነቶቹ ከኩዌት፣ ኬንያ፣ ጋና፣ ሱዳን፣ አልጄሪያ፣ አየርላንድ፣ ጅቡቲ፣ ኮሞሮስ፣ ጋቦን እና ደቡብ ኮሪያ ጋር የተደረጉ ናቸው።
ስምምነቶቹ በዋናነት በአየር ትራንስፖርት አገልግሎት፣ በግብርና ዘርፍ፣ በመንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት፣ በስታንዳርድ የባቡር ሀዲድ መስመር ዝርጋታ፣ በባህል፣ በቱሪዝምና በጠቅላላ ትብብር ዘርፍ ላይ ያተኮሩ ናቸው።
ምክር ቤቱ በስምምነቶቹ ይዘቶች ላይ በስፋት ከተወያየ በኃላ ለአገሪቷ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት እንዲጸድቁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ውሳኔ አሳልፏል።
ምንጭ፦ ኢዜአ