Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የማህበሩ ስራስኪያጅ እና ሂሳብ ሹም በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል በ12 አመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ

0 1,110

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የሌንጮ ማርብል እምነበረድ አምራች የአክሲዮን ማህበር ከ 1 ሚሊየን 704 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ አጭበርብረው ለግል ጥቅም አውለዋል ተብለው በሙስና ወንጀል የተከሰሱት የማህበሩ ስራ አኪያጅ አቶ ቶላ በንቲ እና የማህበሩ ሂሳብ ሹም፤ ዛሬ ረፋድ ላይ በ12 አመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ::

ተከሳሾቹ በፈጸሙት ወንጀል መንግስትን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ያገኝ የነበረውን ከ65 ሺህ ብር በላይ ማሳጣታቸውን የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የአሳሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታውቋል።

በዛሬው እለት የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው ተከሳሾች የሌንጮ ማርብል እምነበረድ አምራቸ አክስዮን ማህበር ስራአስኪያጅ የነበሩት አቶ አቶ ቶላ በንቲ እና 2ኛ ተከሳሽ ደግሞየማህበሩ ሂሳብ ሹም አቶ ፍቃዱ ጉርሜሳ ናቸው።

ተከሳሾቹ በቤኒሻንጉል ክልል በአሶሳ ዞን ኦዳ ቢልጊደሉ ወረዳ ዳሊቲ ቀበሌ ኗሪ ናቸው፡፡

የግል ማህበራት የሙስና ክስ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሰረተው የክልሉ የስነምግባርና ጸረሙስነ ኮሚሽን አቃቢህግ ክስ እንደሚያመላክተው ፥1ኛ ተከሳሽ ከ2005 እስከ 2008 አ/ም በስራ አስኪያጅነት ሲሰሩ ከማህበሩ እምነበረድ ምርት ሽያጭ የተገኘ 1ሚሊየን 619 ሺህ 215 ብር ከ28 ሳንቲም በማጉደል ለግል ጥቅም ማዋላቸው በክሱ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም የኬላ ማለፊያ ደረሰኝ የተቆረጠ በሚል 200 ሺህ ብር ለግል ጥቅም ማዋላቸውን የጠቀሰው የፍርድቤቱ ብይን ፥ በተጠቀሰው የምረትና የሽያጭ ወቅት መንግስትን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ያገኝ የነበረውን ከ65 ሺህ 119 ብር ከ52 ሳንቲም ማሳጣቱ በክሱ ተዘርዝሯል።

ይህ ድርጊት በ1ኛ ተከሳሽ ሲፈጸም 2ኛ ተከሳሽ ሂሳብ ሹም ሆኖ ክትትል ባለማድረጉ ፤የሽያጭ ደረሰኞችን ተባብሮ በማጥፋቱ ምክንያት ለደረሰው ጉዳት ተባባሪ ነው ሲል አቃቢህግ ጠቅሶ ፤ባአጠቃላይ ስራን በማያመች አኳሃን መመራትና ያልተገባ ጥቅም ለማገኘት መሞከር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል።

ተከሳሾቹ ፍርድቤት ቀርበው ድርጊቱን ክደው የተከራከሩ ቢሆንም ፥አቃቢህግ በተከሰሱበት ወንጀል የሰነድና የሰው ምስክር አቅርቦ አሰምታል።

ተከሳሾቹ አቃቢህግ ያቀረበውን የሰነድና የሰውምስክርን መከላከል ባለመቻላቸውም የጥፋተኝነት ብይን ተበይኖባቸዋል።

በዚህም ፍርድቤቱ 1ኛ ተከሳሸ እና 2ኛ ተከሳሽን በተመሳሳይ ቅጣት በ12 አመት ጽኑ እስራትና በ30 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy