Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በስራ ላይ ለሌሉ ከ1 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ደመወዝ እየተከፈለ ነው

0 598

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ግንባታው ቢጠናቀቀቅም እስካሁን ወደ ምርት አልገባም።

ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ የፋብሪካው የግንባታ ሂደትና ለምርት የሚፈለገው የአገዳ አቅርቦት አለመጣጣም ነው።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተንዳሆና በከሰም የስኳር ፋብሪካዎች ያካሄደውን የመስክ ምልከታ ሪፖርት ዛሬ አቅርቧል።

13 ሺህ ቶን አገዳን ፈጭቶ በአመት 3 ሚሊየን ኩንታል ስኳር ያመርታል የተባለው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በአሁኑ ወቅት ስኳር እያመረተ እንደማይገኝ ነው ቋሚ ኮሚቴው ያስታወቀው።

ለዚህም ለፋብሪካው የተዘጋጀው አገዳ ፋብሪካው ተገንብቶ ከመጠናቀቁ በፊት ቀድሞ በመድረሱ ለስኳር ምርት የማይሆን በመሆኑ ነው ብሏል።

ፋብሪካው ሲጠናቀቅ ግን በቂ የአገዳ ምርት ባለመኖሩ በሙሉ አቅም ወደ ምርት መግባት አልተቻለም ነው የተባለው።

ከመስከረም 2010 በኋላ ግን የአገዳ ምርቱ ስለሚደርስ ፋብሪካው ወደ ምርት እንደሚገባ ነው የተነገረው።

በምርት ሂደት ላይ የሚገኘው የከሰም ስኳር ፋብሪካም የአገዳ እጥረት አጋጥሞታል። ፋብሪካው በግንቦት 2007 ዓ.ም የሙከራ ምርት የጀመረ ሲሆን በ2008 ዓ.ም 310 ሺህ ኩንታል ስኳር አምርቷል።

ከሰም በያዝነው አመት 1 ሚሊየን 39 ሺህ ኩንታል ስኳር ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል። ይሁንና የአገዳ እጥረት እንዳጋጠመው ነው የተገለፀው።

ቋሚ ኮሚቴው በሁለቱ የስኳር ፋብሪካዎች ላይ የተከሰተውን ችግር ለመቅረፍ የአገዳ ማሳዎች ተዘጋጅተው አቅርቦቱ መስተካከል እንዳለበት አሳስቧል።

የስኳር ኮርፖሬሽን በበኩሉ ለአገዳው አለመኖርና ለፋብሪካው ስራ አለመጀመር የግንባታዎቹ መዘግየትን በምክንያትነት ጠቅሷል።

በኮርፖሬሽኑ የስትራቴጂካዊ ድጋፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ በዛብህ ገብረየስ እንደገለጹት፥ በአሁኑ ወቅት የአገዳ ማሳዎችን የማልማት እና የማዘጋጀት ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በስራ ላይ ለሌሉ 1 ሺህ 557 ሰዎች ደመወዝ እየተከፈላቸው ይገኛል።

የህዘብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ አባዱላ ገመዳ ለማይሰሩ ሰዎች ደመሞዝ መከፈሉ የፋብሪካውን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ነው ብለዋል።

ድርጊቱ ተቀባይነት የሌለውና የድርጊቱ ፈጻሚዎችም ከተጠያቂነት የማያመልጡ መሆኑንም ነው የተናገሩት።FBC

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy