CURRENT

የታላቁ ህዳሴ ግድቡ የአርማታ ሙሌት 72 በመቶ ተጠናቋል-ኢንጅነር ስመኘው

By Admin

April 02, 2017

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋናው ግድብ የአርማታ ሙሌት 72 በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ገለጹ፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጹን ኢንጅነር ስመኘው በዋናው ግድብ ከሚጠበቀው 10 ነጥብ 2 ሚልዮን ኪዩብ የአርማታ ሙሌት 7 ነጥብ 3 መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡

ከአርማታ ሙሌቱ ጎን ለጎን በግድቡ ቀኝ ክፍል የሚገኙት 10 ዩኒቶችና በግድቡ ግራ ክፍል የሚገኙት 6 ዩኒቶች ፊት ለፊት የሀይል ክፍሎች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ኢንጅነር ስመኘው ተናግረዋል፡፡

በሳድልና ጉባ ተራራዎች ባለው 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ዋና ግድብ ከተገነባ በኃላ 246 ኪ.ሜ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ወደ ኃላ እንዲተኛ ይደረጋል ብለዋል ኢንጅነር ስመኘው፡፡

በግድቡ አማካኝነት የሚጠራቀመው 74 ሚልዮን ኪዩብ ውሃ 16 ዩኒቶች ላይ የተገጠሙ ጄኔሬተሮችን ካንቀሳቀሰ በኃላ ውሃው ወደ ታችኛው ተፋሰስ እንደያልፍ ይደረጋል ብለዋል ስራ አስኪያጁ ኢንጅነር ስመኘው፡፡

ከውሃ መስተላለፊያ ቱቦዎች በተጨማሪ ለታችኛዎቹ ተፋሰስ አገራት 6 ሜትር ስፋት ያላቸው የውሃ ማስተንፈሻ ቱቦዎች በኢፌዴሪ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ እየተገነቡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡