CURRENT

የትግራይ ክልል ምክር ቤት በሚቀጥለው ሳምንት ለክልሉ ተጨማሪ በጀት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል

By Admin

April 08, 2017

የትግራይ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን የፊታችን ማክሰኞ በመቀሌ ያካሂዳል።ምክር ቤቱ በጉባኤው የተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ተጨማሪ በጀቱ ለልማት ስራዎች፣ ለመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ስኬል ማሻሻያ እና ለሌሎች ጉዳይ እንደሚውልም የምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነት እና ኮንፍረንስ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ታረቀኝ ተናግረዋል።በተጨማሪም ጉባኤው የዳኞችን ሹመት ያፀድቃል።