Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ445 ሚሊየን ዶላር ብድር አፀደቀ

0 644

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአለም ባንክ በኢትዮጵያ በከተሞች የውሃ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ እና እና የፍሳሽ አወጋገድ ስርአትን ለማሳደግ የ445 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ብድር አፀደቀ።

ባንኩ በድረ ገፁ ይፋ እንዳደረገው ባንኩ ያፀደቀው ብድር 3 ነጥብ 38 ሚሊየን ኢትዮጵያውያንን የንፁህ ውሃ ተጠቃሚ ያደርጋል።

445 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላሩ በአዲስ አበባ እና 22 አነስተኛ ከተሞች የሚኖሩ ዜጎችን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ለመፍታት እና የከተሞቹን የቆሻሻ አወጋገድ ስርአት ለማሳደግ ይውላል ነው ያለው ባንኩ።

“የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ንፁህ እና አስተማማኝ ውሃ እንዲሁም ዘመናዊ የፍሳሽ አወጋገድ ሊዘረጋ ይገባል” ነው ያሉት በአለም ባንክ የዋተር ግሎባል ፕራክቲስ ስራ አስኪያጅ ዋምቡይ ጊቹሪ።

የአለም ባንክ በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ሰዎች ዋነኛ ፈተና የሆኑትን ውሃ ወለድ እና ከንፅህና ጉድለት ጋር ተያይዘው የሚመጡ በሽታዎችን ለመቀነስ እየሰራ መሆኑንም ስራ አስኪያጇ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የአለም ባንክ ዳይሬክተር ካሮሊን ተርክ፥ ባንኩ ለኢትዮጵያ ያፀደቀው ብድር በከተሞች የንፁህ መጠጥ ውሃ እና የቆሻሻ አወጋገድ ችግርን ለመቅረፍ በሚከናወኑ ስራዎች ለዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑን አንስተዋል።

በኢትዮጵያ የፍሳሽ አወጋገድ ስርአት ያላት ከተማ መዲናዋ አዲስ አበባ ብቻ መሆኗን ባንኩ ጠቁሟል።

ከተማዋ ከፈጣን እድገቷ ጋር ተያይዞ በርካታ የመሰረተ ልማት እየተገነቡባት ቢሆንም በተለይም የቆሻሻ አወጋገድ ስርአቷ ሊዘምን እንደሚገባው ነው የሚነገረው።

በዚህም ሁሉን አቀፍ የከተማ የፍሳሽ አወጋገድ ስርአት ለመዘርጋት የአለም ባንክ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለመስራት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።

ቆሻሻ ውሃን የማከም፣ ያልተማከለ የቆሻሻ አወጋገድ ስርአት መዘርጋት እና የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች መገንባት የአለም ባንክ አዲስ አበባ ከመስፋፋቷ ጋር ተያይዞ እያጋጠማት ያለውን የቆሻሻ አወጋገድ ለማዘመን በመፍትሄነት ያስቀመጣቸው አማራጮች ናቸው።

ምንጭ፦ http://www.worldbank.org/

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy