Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቆሼ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማቋቂም የሚረዳ አደረጃጀት ፈጠረ፡፡

0 447

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቆሼ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማቋቂም የሚረዳ አደረጃጀት ፈጠረ፡፡አደረጃጀቱ ተጐጂዎችን በ6 የሚከፍል ነው፡፡የአስተዳደሩ ከንቲባ ድሪባ በሰጡት መግለጫ በ6 የተከፈው አደረጃጀት፣
ህጋዊ ይዞታ የነበራቸው 16 አባዎራዎችና እማዎራዎች፣ እንዲሁም 13 የእነዚህ ህጋዊ ይዞታ ያላቸው አባዎራዎችና እማዎራዎች ልጆች፣ 54 ተከራዮች ብሎም 1ዐ2 በሸራ እና በጭቃ ቤቶች የሚኖሩ ፣12ዐ በስጋት ቀጠና ውስጥ ያሉ ተነሺዎች እና በአደጋ ወቅት የነፍስ አድን ስራ ይሰሩ የነበሩ የአካባቢው ወጣቶች ናቸው፡፡

የአስተዳደሩ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ግዛው በበኩላቸው ህጋዊ ይዞታ ላላቸው 16 አባዎራዎች እና እማዎራዎች ለእያንዳንዳቸው ቀድሞ በነበራቸው ይዞታ ልክ ምትክ ቦታ ይሰጣቸዋል ብሏል፡፡ህይወት ለጠፋባቸው ወገኖች ለእያንዳንዱ በጠፋው ህይወት ልክ ለቤተሰቦቻቸው 4መቶ ሺ ብር ይሰጣል፡፡የንብረት ካሣም እንደሚከፈልም ተገልጿል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy