የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቆሼ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማቋቂም የሚረዳ አደረጃጀት ፈጠረ፡፡አደረጃጀቱ ተጐጂዎችን በ6 የሚከፍል ነው፡፡የአስተዳደሩ ከንቲባ ድሪባ በሰጡት መግለጫ በ6 የተከፈው አደረጃጀት፣ ህጋዊ ይዞታ የነበራቸው 16 አባዎራዎችና እማዎራዎች፣ እንዲሁም 13 የእነዚህ ህጋዊ ይዞታ ያላቸው አባዎራዎችና እማዎራዎች ልጆች፣ 54 ተከራዮች ብሎም 1ዐ2 በሸራ እና በጭቃ ቤቶች የሚኖሩ ፣12ዐ በስጋት ቀጠና ውስጥ ያሉ ተነሺዎች እና በአደጋ ወቅት የነፍስ አድን ስራ ይሰሩ የነበሩ የአካባቢው ወጣቶች ናቸው፡፡