Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢህአዴግ ምክር ቤት በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቀቀ

0 345

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ያካሄደውን መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቀቀ፡፡

ምክር ቤቱ በጥልቀት የመታደስ የንቅናቄ መድረኮች በተቀመጠላቸው አቅጣጫ መሰረት መፈፀማቸውን ገምግሟል፡፡

በተሃድሶ ንቅናቄው የተጀመረውን ሀገራዊ የህዳሴ ጉዞ ለማሳካት የሚያስችል ሁኔታ ከመፍጠሩም በላይ በአመራርና በአባላት ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት፥ በሲቪል ሰርቫንቱና በህዝቡ ዘንድም የተነሱ ችግሮች እንደሚፈቱ ተስፋ ማሳየቱን ነው የጠቆመው፡፡

የኪራይ ሰብሳቢነት ወኪል የሆኑት የትምክህትና ጠባብነት አመለካከቶችና ተግባራት የፌዴራላዊ ዴምክራሲያዊ ስርዓቱ ዋነኛ አደጋ መሆናቸው ላይ የጋራ መግባባት መደረሱን ምክር ቤቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የትምክህትና ጠባብነት አመለካከቶች በቀጣይ የህዳሴ ጉዞውን ማደናቀፍ ከማይችሉበት ደረጃ ላይ ለማድረስና ሀገራዊ ህዳሴውን እውን ለማድረግ ድርጅቱ፣ ሲቪል ሰርቫንቱ እና ህዝቡ ለለውጥ መነሳሳታቸውን ምክር ቤቱ መገምገሙንም መገለጫው አመልክቷል፡፡

በመንግስት አመራር መልሶ ማደራጀት ላይ ህዝቡ ቀጥተኛና ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ ማድረጉ የስልጣን ባለቤትነቱን ያረጋገጠበት በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ጠቁሟል፡፡

የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን ለማጎልበት በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የተደረጉ ውይይቶች ገንቢ ሚና እየተጨዋቱ ነው ያለው መግለጫው፥ ይህም ሊገባል ብሏል፡፡

ከመልካም አስተዳደር፣ ሙስናና ብልሹ አሰራር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት እየተከናወኑ ያሉትን ስራዎች ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥቶበታል፡፡

የወሰን ማካለል ጉዳይን በአፋጣኝ እልባት ለመስጠት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የጠቆመው የምክር ቤቱ መግለጫ፥ ቀሪ ተግባራት በፍጥነት እንዲከናወኑ ድርጅቱ አቅጣጫ ማስቀመጡን ጠቅሷል፡፡

የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራን በተመለከተ የማሰልጠን፣ የማደራጀት፣ ብድር የማመቻቸትና በተወሰኑ ቦታዎችም ወደ ስራ የማስገባት ተግባራት መከናወናቸውን ገምግሞ፥ በቀጣይ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በትኩረት መከናወን እንዳለበት አሳስቧል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚዊ ጉዳዮች፣ የኢኮኖሚዊና ማሕበራዊ ዘርፎች እንዲሁም በማምረቻ ኢንዱስትሪ ባለፉት ዓመታት እየተመዘገበ የመጣው ፈጣን እና ተከታታይ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በያዝነው ዓመትም ቀጥሏል ነው ያለው መግለጫው፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት የዋጋ ንረቱን በነጠላ አሃዝ ገድቦ ለመያዝ የተደረገው ጥረት ውጤታማ መሆኑንም ነው ያመላከተው፡፡

በያዝነው ዓመት የመኸር ግብርና እድገት በአማካይ 12 በመቶ ማስመዝገብ እንደሚቻልም ትንበያዎች መታየታቸውን ገልጾ፥ በሁሉም አካባቢዎች ህዝቡ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ እና በተፋሰስ ልማት በስፋት እንዲሳተፍ አፅንኦት ሰጥቶበታል፡፡

በሀገራችን ደቡብና ደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ በሰው ህይወት ላይ ሞት በእንስሳት ላይ ደግሞ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በራስ አቅም ለመቋቋም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባልም ብሏል፡፡

በእናቶች እና ህፃናት ጤና እና በትምህርት ጥራት ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን ምክር ቤቱ ገምግሟል፡፡

የመሰረተ-ልማት አቅርቦት ማሻሻል የሚያስችሉ በርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶች በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለማጠናቀቅ ትኩረት ተሰጥቶት ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም አረጋግጧል፡፡

የኢህአዴግ ምክር ቤት “እየታደስን እንሰራለን እየሰራን እንታደሳለን!” በሚል መሪ ሃሳብ ነው ለሁለት ቀናት መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደው፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy