Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያ-ሁናን ኢንዱስትሪ ፓርክ አዳማ ላይ ሊገነባ ነው

0 1,172

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ-ሁናን ሶስተኛው ምዕራፍ የኢንዱስትሪ ፓርክ ከ250 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ አዳማ ላይ ሊገነባ ነው።

የኢንዱስትሪ ፓርኩ የቻይናዋ ሁናን ግዛት ባለሃብቶች ማሽነሪዎች፣ የግንባታና የግብርና መሳሪያዎች የሚያመርቱበት ነው።

የኢትዮጵያና ቻይና የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ዛሬ ሲካሄድ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዶክተር አርከበ ዕቁባይና የሁናን ግዛት ምክትል አስተዳዳሪ ሚስተር ሂ ባኦዢያንግ በፓርኩ ግንባታ ስምምነት ስነድ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል።

ሌሎች ሶስት ስምምነቶችም በኢትዮጵያ መንግስትና በሁናን ግዛት የስራ ኃላፊዎች ተፈርመዋል።

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አርከበ ዕቁባይ የቻይና ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸው ለአገሪቷ ኢንዱስትሪና ለፓርኮች እድገት ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ይላሉ።

የመንግስት አቅጣጫ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ፓርኮችን መገንባት መሆኑን ጠቁመው በአዳማ የሚገነባው ሶስተኛው ምዕራፍ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተለያዩ ማሽነሪዎች የግብርናና የግንባታ መሳሪያዎች አምራቾች የሚሰማሩበት መሆኑን አክለዋል።

በሃዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክ በጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በፋርማሲ ዘርፍ የሚሰማሩ ኩባንያዎች የሚሳተፉ መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል።

የተፈረመው ስምምነት የሁለቱን አገሮች የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር እንዲሁም የሁለትዮሽ ግንኙነት ያሳድጋል ተብሏል።

የሁናን ምክትል አስተዳዳሪ ሚስተር ሂ ባኦዢያንግ ግዛቷ ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ የልማትና ኢንቨስትመንት መስኮች የመስራት ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።

ስምምነቱ የግዛቷ ባለሃብቶች የኢትዮጵያን መንግስት ድጋፍና ማበረታቻ ተጠቅመው በኢንዱስትሪ፣ በግብርናና ሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሰማሩ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሲሳይ ገመቹ በአዳማ የሚገነባው “ኢትዮጵያ-ሁናን ኢንዱስትሪ ፓርክ” ከቻይና ኤግዚም ባንክ በተገኘ ብድር እንደሚከወን ጠቁመዋል።

ግንባታው በ122 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን ከ12 እስከ 18 ወራት በሚፈጅ ጊዜ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ 365 ሄክታር የሚሸፍን ሲሆን በመጀመሪያው ምዕራፍ የአልባሳት፣ በሁለተኛው የጨርቃጨርቅና የሁናን ግዛት ድርጅቶች የሚሳተፉበት ሶስተኛው ምዕራፍ ደግሞ የተለያዩ ማምረቻ፣ መገልገያ፣ የግብርናና የግንባታ መሳሪያዎች ይመረቱበታል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy