Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ተጠሪነት ወደ ንግድ ሚኒስቴር ተዛወረ

0 871

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ተጠሪነት ወደ ንግድ ሚኒስቴር እንዲዛወር ወሰነ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 27ኛ መደበኛ ጉባዔ በሁለት አዋጆችና ሶስት ደንቦች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ተጠሪነት የተቀየረበት ዋነኛ ምክንያትም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ከጉዳዩ ጋር አግባብ ካላቸው የዘርፉ መስሪያ ቤቶች ጋር ለማቀናጀት እንዲያመች መሆኑ ተገልጿል።

እንዲሁም የኢትዮጵያ ምርት ገበያና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ካፒታልን ለማሳደግ የቀረበውን ጥያቄ የተቀበለ ሲሆን ለማሻሻያ የቀረቡ ረቂቅ ደንቦች በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው እንዲወጡና በስራ ላይ እንዲውሉ ወስኗል።

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ግብርና ምርቶች መጋዘን አገልግሎት ድርጅት ፈርሶ የድርጅቱ አገልግሎት ከግብይት ስራ ጋር ተጨምሮ መብትና ግዴታው ለኢትዮጵያ ምርት ገበያ እንዲተላለፍ ወስኗል።

ይህም በግብይት ሰንሰለት ላይ የሚታዩ የተጋነኑ ወጪዎችን ለማስቀረትና የአይ ሲ ቲ መሠረተ ልማትን በጋራ በመጠቀም የገበያ መረጃ ቅብብሎሽን ለማሳለጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል።

ምክር ቤቱ በመጨረሻም የብሔራዊ ስነልክ ኢንስቲትዩት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የክፍያ ተመን ረቂቅ ደንብን ተመልክቷል።

በዚህ ስራ ላይ የሚሰማሩ ባለሙያዎች የብቃት ማረጋገጫ መስጠትና የልኬት መሳሪያዎቹን በየጊዜው በመፈተሽ ጤናማ የንግድ ስርዓት እንዲኖር እንደሚያግዝ ነው የጠቆመው።

በዚህም መሠረት ረቂቅ ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እንዲወጣና በስራ ላይ እንዲውል መወሰኑን ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy