Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያ ፈጣን እድገት ለአፍሪካ አገራት ተምሳሌት ነው – የኡጋንዳ ወታደራዊ ኮሌጅ አዛዥ

0 379

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች እያስመዘገበች ያለችው ፈጣን እድገት ለአፍሪካ አገራት ተምሳሌት መሆኑን የኡጋንዳ ወታደራዊ ኮሌጅ አዛዥ ኮማንዳንት ሌተናል ጄኔራል አንድሪው ጉቲ ገለፁ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ አባ ዱላ ገመዳ ከኡጋንዳ ወታደራዊ ኮሌጅ ለመጡ 26 አዛዦችና ተማሪዎች አገሪቷ እያስመዘገበች ያለችውን እድገት አስመልክቶ በጽህፈት ቤታቸው ገለፃ አድርገውላቸዋል።

የኡጋንዳ ወታደራዊ ኮሌጅ ኮማንዳንት ሌተናል ጄኔራል አንድሪው ጉቲ አገሪቷ በተለይም በምስራቅ አፍሪካ የኢንዱስትሪና የማምረቻ ማዕከል ለመሆን የምታደርገው ጥረት አስደናቂ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በአካባቢያዊና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች በጋራ እየሰሩ መሆኑን ገልጸው በሠላምና ፀጥታ ጉዳይ በጎረቤት አገራት ሶማሊያና ደቡብ ሱዳን የሚያከናውኑትን የሠላም ማስከበር ተግባር አንስተዋል።

የወታደራዊ ኮሌጁ ተማሪዎችም አገሪቷ እያስመዘገበች ካለው ዕድገት ባሻገር ከአፍሪካ ግዙፍ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬት እንዳስደነቃቸው ተናግረዋል።

አፈጉባዔ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው የአገሪቷ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ዋነኛ መሰረት የኅብረተሰቡን ተሳትፎ ማረጋገጥና የዴሞክራሲ ተቋማት መገንባታቸው መሆኑንን ገልጸውላቸዋል።

በአገሪቷ የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች የህዝቡ ንቁ ተሳትፎ ባይታከልባቸው ውጤቶች ሊመዘገቡ አይችሉም ነበር ሲሉም አክለዋል።

ኡጋንዳ የአካባቢውን ሠላም ለማስከበር የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን የጠቀሱት አፈ ጉባዔው በጎረቤት አገራት ሶማሊያና ደቡብ ሱዳን በሠላም ማስከበር ዘርፍ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ለአብነት አንስተዋል።

በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና የባህል ልውውጥ ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል።

“የስደተኞች ፍልሰት የሁለቱ አገራት የጋራ ችግር ነው” ያሉት አፈጉባዔ አባዱላ ችግሩን ለመፍታት በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያና ኡጋንዳ የሁለትዮሽ ግንኙነት በ1970 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ኢትዮጵያ በ1995 በኡጋንዳ የቆንሲላ ጽህፈት ቤት፣ በ1996 ዓ.ም ደግሞ ኢምባሲዋን ከፍታለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ይለማሪያም ደሳለኝ በቅርቡ በኡጋንዳ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy