NEWS

የኢትዮ-ጃፓን የቢዝነስ ፎረም ዛሬ በቶኪዮ ይካሄዳል

By Admin

April 25, 2017

የኢትዮጵያ እና የጃፓን የቢዝነስ ፎረም ዛሬ በቶኪዮ ይጀመራል፡፡

በኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ አብተው የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክም ጃፓን ገብቷል፡፡

ፎረሙ በማምረቻ ኢንዱስትሪ እድገት ላይ አተኩሮ እንደሚመክር ተጠቁሟል፡፡

በኢትዮጵያ እያደገ የመጣው የማምረቻ ኢንዱስት ዘርፍ እና የተቀናጀ የግብርና ምርት ማቀነባበር ላይ የኢትዮጵያ እና የጃፓን ትብብር ለዘርፉ እድገት በሚኖረው አስተዋፅኦ ላይ ውይይት ይደረጋልም ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ እና ጃፓን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን የሚያጠናክር አዲስ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና የጃፓኑ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ናቸው ስምምነቱን የተፈራረሙት፡፡

ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስር እና የንግድ ዲፕሎማሲ ቀጣይ እንዲሆን እና እንዲጠናከር አዲስ በር ከፋች ነው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አፈወርቅ፥ የመግባቢያ ስምምነቱ የሁለቱ ሀገራት የንግድ ማህበረሰብ ተግባራዊ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ትስስር እና ተጠቃሚነት እንደ አዲስ የሚፈጥሩበት ነው ብለዋል፡፡

የጃፓን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቶሩ ኢሺዳ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ በሰው ሃይል ልማት ላይ እየሰራች መሆኗን አድንቀዋል፡፡

ስምምነቱ በሁለትዮሽ የንግድ ስርዓቱ እና በኢንቨስትመንት ላይ መረጃዎችን ለመለዋወጥና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመለየትና በጋራ ለመፍታት እንደሚያስችል ነው የተነገረው፡፡