Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኦህዴድ 27ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ማጠቃለያ እየተከበረ ነው

0 427

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አዲስ አበባ ሚያዝያ 1/2009 የኦህዴድ 27ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ማጠቃለያ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተከበረ ነው።

የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ኦህዴድ የኦሮሞን ህዝብ ትግል ወደሌላ ምዕራፍ ያሸጋገረ መሆኑን ተናግረዋል።

የኦሮሞ ህዝብ አሁንም ጥያቄዎች አሉት ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ ድርጅቱ ጥያቄዎቹን ለመመለስ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ባለፉት 27 ዓመታት የተሰሩ ስራዎች እንዳሉ ሆነው “ከፊታችን የሚጠብቀንን ትግል በቁርጠኝነት ለማለፍ በተሃድሶ ውስጥ አልፈን ለህዝቡ ቃላችንን አድሰናል” ብለዋል።

በመሆኑም አሁን ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ እየተንቀሳቀስን ያለንበት ጊዜ ነው ሲሉም አክለዋል።

ዶክተር ወርቅነህ ለድርጅቱ አባላት፣ ለኦሮሞ ህዝብና ለእህት ድርጅቶች ባስተላለፉት መልዕክት እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከኦህዴድ ጎን እንዲሰለፉ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy