Artcles

የዴሞክራሲ ማሳለጫ ተቋማት አቅም እየጎለበተ መምጣቱ ምንን ያሳያል?

By Admin

April 30, 2017

የዴሞክራሲ ማሳለጫ ተቋማት አቅም እየጎለበተ መምጣቱ ምንን ያሳያል?/ ቶሎሳ ኡርጌሳ/

                       ሀገራችን የምትከተለው ስርዓት ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ነው’ ሲባል፤ እንዲያው ለማለት ያህል አሊያም ለታይታ ተብሎ የሚነገር ሃቅ አይደለም። በልማቱም ይሁን በዴሞክራሲው መስክ ሁለንተናዊ ለውጦችን የሚያስመዘግብ ሥርዓት መሆኑ በተግባር የታየ ስለሆነ ነው። እናም በርዕሴ ላይ ወዳነሳሁት የዴሞክራሲ ማሳለጫ ተቋማት አቅም የመጎልበት ጉዳይ ከማቅናቴ በፊት፤ በቅድሚያ ስለ ልማታዊ ዕድገታችን ጥቂት ማለት አስፈላጊ ነው—ነገሩ አንዱን ጥሎ ሌላውን አንጠልጥሎ እንዳይሆንብኝ።

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ልማታዊነት በተለይም ባለፉት 15 ዓመታት ውስጥ ፈጣንና ተከታታይ ሆኖ እያደገ ተምሳሌታዊ መሆን የቻለ ነው። ዓለም በልማት እየተመሙ ያሉትን እንደ ማሌዥያ፣ ህንድ፣ ሲንጋፖርን…የመሳሰሉ የኤሽያን ሀገራት “ኤሽያን ታይገርስ” (የኢስያ ነብሮች) እያለ ይጠራቸዋል። የእኛዋ ኢትዮጵያም ባስመዘገበችው ምሳሌያዊ የልማት ዕድገት “አፍሪካን ታይገር” (አፍሪካዊ ነብር) የሚል ስያሜ ተችሯታል። ነዳጅ ከሌላቸው የሰሃራ በታች ሀገራት ውስጥ ፈጣንና ተከታታይ ዕድገት በማስመዝገቧ ነው ይህ ስያሜ የተሰጣት።

በልማት ጎዳና እየተመመች ያለችው አዲሲቷ ኢትዮጵያ በ“ነብር” መመሰሏ አንድ የሀገራችንን ይትብሃል ያስታውሰኛል—“የነብርን ጭራ አይዙም፤ ከያዙም አይለቁ” የሚለውን። አዎ! የነብርን ጭራ ሲጀመር አጥብቀው ካልያዙትና በተወሰነ የጊዜ ቆይታ ከለቀቁት ተመልሶ በነብሩ መበላትን ያስከትላል ለማለት ነው— የሀገራችን ህዝብ ይህንን አባባል የሚጠቀመው። ርግጥም በነብር የተመሰለውን የልማት ዕድገት አንዴ አለመያዝ እንጂ ይዘውት ከተለለቀቀ፤ ቀደም ሲል ከልማቱ በየደረጃው ሲጠቀም የነበረው ህዝብ መልሶ መጠየቁና ሌላ ፈጣንና ተከታታይ ልማት የሚያስመዘግብ ኃይልን መሻቱ የሚቀር አይሆንም። ታዲያ የሀገራችን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስትና የልማቱ ዋነኛ ተዋናይ የሆኑት የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ይህን ልማታዊ “የነብር ጭራ” በደንብ አጥብቀው ከያዙበት ከዛሬ 15 ዓመት በፊት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አልለቀቁትም። አለመልቀቅ ብቻ ሳይሆን ዓለም የመሰከረለትን ዕድገት አስመዝግበዋል። ወደፊትም ይህን “የነብር ጭራ” እንደማይለቁ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ተንብዩዋል። ድርጅቱ በቀጣዩ ዓመት የዓለም ምጣኔ ሃብት እንደሚያድግ ሰሞኑን በተነበየበት ሪፖርቱ ላይ፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት በተረጋጋ ሁኔታ እንደሚቀጥል አስታውቋል። ይህም የተያዘው ልማታዊ ዕድገት ነገም ሆነ ከነገ ወዲያ የማይለቀቅ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ስለ ልማታዊ ዕድገቱን ይህን ያህል በጨረፍታ ካልኩ ዘንዳ፤ አሁን ደግሞ በርዕስነት ወደያዝኩት የዴሞክራሲ ማሳላጫ ተቋማት አቅም ማደግ ሁኔታ ላምራ።…

ዴሞክራሲ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ “የሞት ሽረት” ጉዳይ መሆኑ ተደጋግሞ ተገልጿል። ይህ የሆነውም ሀገራችን የምትከተለው የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ስለሆነ ነው። እርግጥ ማንኛውም ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ከእንከኖች የፀዳ ነው ተብሎ አይታሰብም። በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ያለ ባለፉት ፊውዳላዊና አምባገነናዊ ስርዓቶች የራሳቸውን ፀረ-ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰቦችን ትተው ያለፉባት ጀማሪ የዴሞክራሲ አራማጅ ሀገር የዴሞክራሲ ባህል ግንባታው በተፈለገው ፍጥነት ሊሄድ እንደማይችል እሙን ነው። ታዲያ ይህን ችግር ለመፍታት ሥርዓቱ ራሱን በራሱ የሚያርምበት የዴሞክራሲ ማሳለጫ ተቋማትን አቋቁሟል። ከእነዚህ ተቋማት ውስጥ የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት፣ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ መገናኛ ብዙሃን፣ ሲቪክ ማህበራት…ተጠቃሽ ናቸው።

እነዚህ ተቋማት ቀደም ሲል በጠቀስኳቸው በሀገራችን ውሰጥ ባለፉት ስርዓቶች ሳቢያ ሲንከባለሉ የመጡት ፀረ-ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰሶች እንዲሁም ከተቋማቱ የአቅም ውስንነት አኳያ የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ ሚና ተወጥተዋል ለማለት አያስደፍርም። ይሁንና ማንኛውም አስተሳሰብና አቅም በጊዜ ሂደት ውስጥ የሚጎለብት በመሆኑ፤ ተቋማቱ ከትናንት በስቲያ ትናንት፣ ከትናንት ዛሬ፣ ከዛሬ ደግሞ ነገና ከነገ ወዲያ አሰራራቸው መዘመኑ ብሎም አቅማቸውም መጎልበቱ የሚቀር አይደለም። የኢፌዴሪ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በተለያዩ ወቅቶች በሀገሪቱ በሚከሰቱ ችግሮች ሳቢያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመመርመር ከትናንት ዛሬ አቅሙ መጎልበቱን መገንዘብ (በአንዳንድ የኦሮሚያና የአማራ አካባቢዎች የተከሰተውን ችግር በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ያቀረበውን ሪፖርት ያስታውሷል!) እንዲሁም የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈፃሚው አካል ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር፣ ክትትልና ድጋፍ ማየት የሚቻል ይመስለኛል። እነዚህ በምሳሌነት ያነሳኋቸው የዴሞክራሲ ማሳለጫ ተቋማት አቅማቸው እየጎለበተ የመጣ ቢሆንም፤ በዚህ ፅሑፍ ግን በኢፌዴሪ ህገ መንግስት ከአንቀፅ 54 እስከ አንቀፅ 59 ድረስ በተቀመጠው ድንጋጌ መሰረት የተቋቋመው፣ ስልጣንና ኃላፊነት የተሰጠው እንዲሁም ተግባሩን የሚወጣውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን እንደ ማሳያ ለማቅረብ እሞክራለሁ። ይህም በእኔ እምነት የተቋማቱ አቅም በየጊዜው መጎልበቱ የሚያመላክተው ነገር አለ። እርሱም የሀገራችን ዴሞክራሲ በጊዜ ዑደት ውስጥ እያበበና እየጎለበተ መምጣቱን የሚያሳይ ይመስለኛል።

እንደሚታወቀው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ዴሞክራሲያዊ የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤትን (ፓርላማን) ይወልዳል። በህዝብ ተመራጭ የሆነ የፖለቲካ መስመርም የሀገሪቱን ፖሊሲዎችንና ዕቅዶችንም የመምራት መብት ያለው መሆኑም እንዲሁ። ታዲያ በየትኛውም ሀገር ውስጥ የሚገኝ ገዥ ፓርቲ ይህን መብት የሚያገኘው፣ መብቱ ከሞላ ጎደል በሁሉም ዴሞክራሲያዊ ህገ-መንግስቶች ውስጥ የሚሰፍር አንቀፅ ስለሆነ ብቻ አይደለም። ከዚያ ይልቅ እንደኛ ያሉ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት የሚከተሉ ሀገሮች ገዥ ፓርቲዎች ይህን ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ ገቢራዊ የሚያደርጉት፤ በፓርላማ አብላጫ ወንበር ስላላቸውና የጠራ መስመር በመከተላቸው ምክንያት በድምፅ ብልጫ ሁሌም ስለሚያሸንፉ ይመስለኛል። ይሁንናዳሩ ግን በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ ገዥ ፓርቲዎች አብላጫ ወንበር ስላላቸውና ህጋዊ እስከሆኑ ድረስ የፈለጉትን ጉዳይ በፓርላማ ማሳለፍ ስለሚችሉ ብቻ ሁሉንም ነገር አይከውኑም። ሀገራችን ውስጥ በመገንባት ላይ የሚገኘው ፓርላሜንታዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትም ይህን አካሄድ በጥብቅ የሚያምንና የሚከተል መሆኑን መገንዘብ የሚገባ ይመስለኛል።

መንግሥትም ይህን አሰራር እውን አድርጎ ወደ ተግባር ከተረጎመ እነሆ 26 ዓመታትን ሊደፍን ከአንድ ወር ያነሰ ጊዜ ብቻ ይቀረዋል። ይህን ዕውነታ መገንዘብ የማይሹት ፅንፈኛ ሃይሎች ግን ሁኔታውን በተገላቢጦሽ በመመልከት ‘የአንድ ፓርቲ የበላይነት የሰፈነበት ፓርላማ ስራ አስፈፃሚውን ሊቆጣቀጠረው አይችልም’ የሚል አስተሳሰብን ሲየራምዱ ይስተዋላል። በእኔ እምነት ይህ አስተሳሰብ ፈፅሞ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚሄድ አይደለም። አስተሳሰቡ ትክክል አለመሆኑንም ፓርላማው አቅሙን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጎለበተ በመምጣት አስፈፃሚው አካል ላይ የሚያካሂዳቸው በሚያካሂዳቸው ቁጥጥርና ክትትል ብሎም የድጋፍ ስራዎች የሚያረጋግጡ ይመስለኛል።

በእኔ እምነት በየትኛውም ዴሞክራሲን በሚከተል ሀገር ውስጥ ስራ አስፈፃሚውን የመቆጣጠር ስራ የሥርዓቱ ተግባር ነው። ራሱንም እንደ መስታወት መለስ ብሎ የሚያይበት አሰራር ነው። እናም ምንም እንኳን እዚህ ሀገር ውስጥ የጠራ መስመር ያለውና ህዝብን ሊያማልል የሚችል ፖሊሲን የሚያራምድ ተቃዋሚን ለማየት ባንታደልም፤ ፓርላማው ውስጥ ተቃዋሚዎች ስለሌሉ ብቻ ‘ፓርላማው የአንድ ፓርቲ ስብስብ ስለሆነ ስራ አስፈፃሚውን አይቆጣጠረውም’ ብሎ ማሰብ አስገራሚ ብቻ ሳይሆን፤ ፓርላማው እያከናወነ ያለውን ጠንካራ የቁጥጥር ስራዎችንም እየሰሙ እንዳልሰሙ በመሆን “ጆሮ ዳባ ልበስ” ማለትም ጭምር ነው።

ዚህ ላይ ሀገራችን ውስጥ ጠንካራ ተቃዋሚዎች ቢኖሩ ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓቱ ምንም ዓይነት ፋይዳ የለውም እያልኩ አለመሆኑ ሊታወቅልኝ ይገባል። ጠንካራ ተቃዋሚዎች በአንድ ሀገር የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ላይ ሊኖራቸው የሚችለው ወሳኝ ሚና ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ዓይነት ነውና። እናም ጠንካራ ተቃዋሚዎች ቢኖሩን እሰየው ነው። ከሌሉን ደግሞ ውሳኔው የስልጣን ባለቤት የሆነው ህዝብ ነውና ምንም ማድረግ አይቻልም። ያም ሆኖ ግን ተቃዋሚዎች ፓርላማው ውስጥ ስለሌሉ ፓርላማው ስራ አስፈፃሚውን አይቆጣጠረውም ብሎ ማሰብ ተገቢ አይደለም። ተቃዋሚዎች ፓርላማው ውስጥ ስለሌሉ የህዝብ ችግሮችና ብሶቶች ተድበስብሰው የሚቀሩበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይችልም። ሌላው ቀርቶ ሰሞኑን ፓርላማው የአስፈፃሚውን አካል የሆኑ አንዳንድ መስሪያ ቤቶችን በመስክ ቅኝት ሲመለከት ያገጠሙትን ሁኔታዎች ለፓርላማው ሲያቀርብ ውሳኔዎች እየተላለፉ መሆናቸውን እዚህ ላይ መጥቀስ የሚቻል ይመስለኛል።

በፓርላማው የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ በአፋር ክልል በሚገኙ የፌዴራል መንግሥት ተቋማት ላይ ያደረገውን የመስክ ምልከታ ተከትሎ አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ በጂቡቲና በደረቅ ወደቦች የተከማቹ ንብረቶችና ባለቤቶች ላይ የኦዲት ምርመራ እንዲያከናውን ውሳኔ ከመስጠታቸው ባሻገር፤ የምርመራ ውጤቱ በተጠያቂነት የሚለያቸው የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንዲወሰድ ፓርላማው ለመንግሥት እንደሚያቀርብ አስታውቀዋል።

ይህ ሁኔታም የዴሞክራሲ ማሳለጫ ተቋም የሆነው ፓርላማ በሂደት አቅሙ እየጎለበተ፣ ለአስፈፃሚው አካል ከሚያደርገው ድጋፍ ባሻገር አጥፊዎች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለመንግሥት እስከ ማቅረብ ድረስ የዘለቀ መሆኑን የሚያሳይ ተግባር ይመስለኛል። ፓርላማው አቅሙ በጎለበተ ቁጥር የህዝብ ወኪልነቱን በተገቢው መንገድ እንደሚያረጋግጥ የሚያመላክት ነው። የዴሞክራሲ ሥርዓት ባህል ገንቢነታችም ስር በመስደድ ላይ መሆኑንም ያሳያል። ታዲያ እንደ ፓርላማው ዓይነት የዴሞክራሲ ማሳለጫ ተቋማት አቅማቸው እየጎለበተ ሲመጣ ዴሞክራሲው ከነበረበት የስልጠት ቦታ አንድ እርምጃም ቢሆን ፈቀቅ ስለሚያደርጉት አቅማቸው እንዲጎለብት ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል። የተቋማቱ አቅም መጎልበት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታውን የሚያፋጥን፣ የአስፈፃሚውን አካል አሰራሮች የሚነቅስና የሚደግፍ፣ በዚያኑ ልክም የህግ የበላይነትንና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን በመሆኑ አቅማቸው ይደግ፤ ይጎልብት እላለሁ።  

                                                      ቶሎሳ ኡርጌሳ

‘ሀገራችን የምትከተለው ስርዓት ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ነው’ ሲባል፤ እንዲያው ለማለት ያህል አሊያም ለታይታ ተብሎ የሚነገር ሃቅ አይደለም። በልማቱም ይሁን በዴሞክራሲው መስክ ሁለንተናዊ ለውጦችን የሚያስመዘግብ ሥርዓት መሆኑ በተግባር የታየ ስለሆነ ነው። እናም በርዕሴ ላይ ወዳነሳሁት የዴሞክራሲ ማሳለጫ ተቋማት አቅም የመጎልበት ጉዳይ ከማቅናቴ በፊት፤ በቅድሚያ ስለ ልማታዊ ዕድገታችን ጥቂት ማለት አስፈላጊ ነው—ነገሩ አንዱን ጥሎ ሌላውን አንጠልጥሎ እንዳይሆንብኝ።