CURRENT

የጉዞ ፍቃድ የወሰዱ 2 መቶ ኢትዮጵያዊያን አዲስ አበባ ገብተዋል፡- ውጭ ጉዳይ

By Admin

April 20, 2017

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ያወጣውን አዋጅ ተከትሎ እስከ አሁን ድረስ በህገ ወጥ መልኩ የሚኖሩና የጉዞ ሰነድ ያወጡ 2 መቶ ኢትዮጵዊያን ወደ አገር ቤት መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አስታውቋል፡፡

አዋጁን ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት የሚመለሱ ዜጎች የግል መገልገያ ዕቃዎቻቸውን ከማንኛውም ቀረጥና ታክስ ነፃ በሆነ መንገድ ወደ አገር ቤት እንዲያስገቡ መፍቀዱንም የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል፡፡

ዜጎች ይኖሩበት ከነበረው ሳዑዲ ዓረቢያ  ሲወጡ ይዘዋቸው የሚመጡት የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ የጋዝ ምድጃ፣ ቴሌቪዥን፣ ኮምፒውተር 21 ዓይነት የግል መገልገያ ዕቃዎችን ይዘው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተፈቅዶላቸዋል፡፡

ሳውዲ አረቢያ ያለመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ የሚኖሩ የውጭ ሀገራት ዜጎች በ90 ቀናት ያለቅጣት አገሪቱን ለቀውእንዲወጡ  ያወጣቸውን  አዋጅ ተከትሎ የሁሉም አገራት ዜጎች ናቸው ወደየአገሮቻቸው አየተመለሱ ያሉት፡፡

የሳውዲ መንግስት ህገወጥ የሚላቸው በህገወጥ መንገድ የሳውዲን ደንበሮች አቋርጠው የገቡ ስደተኞች፣ ቋሚ ቦታ ሳይኖራቸው በመዘዋወር በህገወጥ መንገድ የሚሰሩ ስደተኞች፣ የስራ እና የመኖሪያ ፈቃድ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ የውጭ አገር ነዋሪዎች፣ የስራ ፈቃድ ኖሮት ነገር ግን የመኖሪያ ፈቃድ መታወቂያ ካርድ የሌላቸው የውጭ አገር ዜጎች ነዋሪዎች፣ ለኡምራና ሃጂ ሂደው በዚያው የቀሩ/ የቆይታ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ነዋሪዎች፣ እና ያለ ሀጂ ፈቃድ የተጓዙ አማኞች ዋነኛዎቹ ናቸው፡፡

በአዋጁ የተሰጠውን የጊዜ ገደብ አክብረው ለሚወጡ የውጭ አገር ዜጎች መከናወን የሚገባቸው ጉዳዮች፥

ከምህረት ጊዜው መጠናቀቅ በኋላ ለህገ ወጦቹ ከለላ የሰጠ ወይም የቀጠረ ማንኛውም ግለሰብ ሆነ የንግድ ተቋም በሀገሪቱ በወጡት የወንጀል ህጎች እንደሚጠየቅና የእስራትና ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እንደሚያስከትልበአዋጁ  ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚስቴር