Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዩናይትድ ስቴትስ በኤርትራ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጣለች

1 624

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ዩናይትድ ስቴትስ በኤርትራ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ መጣሏን ይፋ አደረገች። ኤርትራ ተጨማሪ ማዕቀብ የተጣለባት ከሰሜን ኮርያ ወታደራዊ የመገናኛ ራዲዮ መግዛቷ ከተደረሰበት በኋላ ነው።ሰሜን ኮርያ ላይ የወታደራዊ ቁሳቁስ ግዥና ሽያጭ ማዕቀብ ከተጣለ አመታት ተቆጥረዋል።

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከኤርትራ ባህር ሀይል ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ላለማድረግ የወሰነበትን የማዕቀብ ውሳኔ ሰነድ ይፋ አድርጓል።በሰነዱ እንደተመለከተው ኤርትራ በቻይና በኩል ከሰሜን ኮሪያ የገዛቻቸው የመገናኛ ራዲዮ መሳሪያዎች ለባህር ሀይሏ አገልግሎት እንዲውሉ የታሰቡ ናቸው።

ኤርትራ ከሰሜን ኮርያ ወታደራዊ ቁሳቁስ ስትገዛ ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም።
መሳሪያዎቹ የተገዙት በፈረንጅ አቆጣጠር 2016 ሲሆን ጉዳዩ በመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ባለፈው ወር ይፋ ባደረገው ሰነድ ሰለ ህገ ወጥ ግዥው ተብራርቷል። ኤርትራ በሶማሊያ ያሉ ታጣቂዎችን ትደግፋለች በሚል ማዕቀብ ከተጣለባት ስምንት አመታት ሆኗል። አስመራ ማዕቀቡ ፍርደ ገምድል ነው ስትል ትቃወማለች። ማዕቀቡን የሚያብራራውን ስነድ በማስፈንጠሪያው ያገኙታል-  https://www.gpo.gov/fdsys/pkg/FR-2017-03-30/html/2017-06225.htm

  1. Minychil Desta says

    Meaning less. It should destroy the whole rotten government and there must safe and democrat gov for the people of Eritrea !

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy