Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዴንማርክ በሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች

0 352

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ዴንማርክ የኢትዮጵያ መንግስት በሳዑዲ ዓረቢያ የሚኖሩ ዜጎቹን ወደ አገራቸው ለመመለስ የጀመረውን ተግባር እንደምትደግፍ ገለጻለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ፥ የዴንማርክ የስደተኞች ኢንተግሬሽንና ቤቶች ሚኒስትር ሚስ ኢንገር ስቶይበርግን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሚኒስትር ዲኤታዋ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት የሚመጡ ስደተኞችን እያስተናገደች መሆኑን ጠቅሰው፥ ከማስጠለልና አስፈላጊውን ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር በትምህርት ተቋማት ገብተው እንዲማሩ እያደረገች ነው ብለዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረትና አፍሪካ የጋራ የስደተኞች አጀንዳ ፕሮግራምና ሌሎች የትብብር ማዕቀፎችን ተፈጻሚ በማድረግ ሀገራቱ በስደተኞች ጉዳይ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር እንደሚችሉም አስረድተዋል።

ዴንማርክ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ስደተኞች እያደረገች ላለችው ድጋፍ አመስግነው ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የዴንማርክ የስደተኞች ኢንተግሬሽንና ቤቶች ሚኒስትር ሚስ ኢንገር ስቶይበርግ በበኩላቸው፥ ሀገራቸው የኢትዮጵያ መንግስት በሳዑዲ ዓረቢያ የሚኖሩ ዜጎቹን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እያከናወነ ላለው ተግባር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል።

ከሳዑዲ የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው ማህበራዊ ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ድጋፍ ታደርጋለች ነው ያሉት ሚስ ኢንገር።

ትናንት በሰሜኑ የሀገሪቷ ክፍል የሚገኝ የስደተኞች መጠለያ መጎብኘታቸውን ጠቅሰው ይህም የስደተኞችን አያያዝና እንክብካቤ ለማወቅ እንደረዳቸው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ለስደተኞች የምታደርገውን ድጋፍ ያደነቁ ሲሆን ዴንማርክ በቀጣይ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።

ሁለቱ ሀገራት በኃይል አቅርቦት፣ በግብርና፣ በሰብዓዊ መብት ጉዳዮችና በቤት ውስጥ ፆታዊ ጥቃት መከላከል ላይ በቅርበት ይሰራሉ።

ዴንማርክ በዓለም አቀፉ የልማት ትብብር ኤጀንሲዋ ዲ ኤ ኤን አይ ዲ ኤ አማካኝነትም ለኢትዮጵያ ድጋፍ ታደርጋለች።

ኢትዮጵያና ዴንማርክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1960 መሆኑን የኢዜአ ዘገባ ያሳያል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy