NEWS

ጠበቃ ሳይቆምለትና በቀረበበት ክስ ላይ ክረክር ሳይደረግበት በ11 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት ግለሰብ የቅጣት ውሳኔ ተሻረ

By Admin

April 17, 2017

ጠበቃ ሳይቆምለትና በቀረበበት ክስ ላይ ክረክር ሳይደረግበት በ11 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት ግለሰብ የቅጣት ውሳኔ ተሻረ።

ውሳኔውን የሻረው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲሆን፥ የቅጣት ውሳኔው የተላለፈው በ2008 ዓመተ ምህረት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነበር።

ተከሳሽ የኋላመር አየለ በተራ የሰው መግደል ወንጀል ተከሶ ፍርድቤት ቀርቦ ድርጊቱን አልፈጸምኩም ብሎ ተከራክሮ ነበር።

ሆኖም ግን ፍርድ ቤቱ ለተከሳሹ ጠበቃ ሳያቆም ክርክር ሳይደረግበትና በችሎቱ የሰው ምስክር ሳይሰማ የመጀመሪያ የምርመራ የምስክር ቃልን መነሻ በማድረግ በ11 ጽኑ እስራት እንዲቀጣና ማረሚያ ቤት እንዲገባ ማድረጉን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጠቅሷል።

ጉዳዩን የተመለከተው ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ምስክርና ትክክለኛ ማስረጃ በፍርድ ቤት ሳይቀርብ ለግለሰቡ ጠበቃ ሳይቆምለት በ11 አመት ጽኑ መቅጣቱ ተገቢ አደለም ሲል ውድቅ አድርጎታል።

ተከሳሹ በጠበቃ ተወክሎ በድጋሚ ከመጀመሪያው ጀምሮ ተመልሶ ጉዳዩ እንዲታይለት ተወስኗል።