Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ፀሎተ ሃሙስ ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ስነስርዓቶች ተከበረ

0 3,135

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በዛሬው እለት የፀሎተ ሃሙስ በዓል በኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንና በኢትዮጽያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በፀሎት፣ በስግደት በህጽበተ እግር እና በተለያዩ መንፈሳዊ ስርዓቶች ተከብሮ ውሏል።

በዓሉ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ሲከበር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፥ ከርስቶስ ዝቅ ብሎ የሃዋርያቱን እግር ማጠቡን ለማጠየቅ የሊቃነ ጳጳሳቱን እግር አጥበዋል።

ሊቃና ጳጳሳቱም የቆሞሳት እና ካህናትን፣ ካህናቱም የምእመናኑን እግር በማጠብ ትህትናን አሰተምረዋል።

ክርስቶስ ትህትናን ለማስተማር ሲል ዝቅ ብሎ የሃዋርያቱን እግር እንዳጠበ ሁሉ በፍቅር በመተባበርና በፍጹም ትህትን እርስ በእርስ መከባበር እንዳለባቸው የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ አስተምረዋል።

በተመሳሳይ በዓሉ በካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ በልደታ ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ስነ ሰርኣቶች ሲከበር፥ ብፁእ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘ ካቶሊካውያን የቀሳውስቱን እና የምእመናንን እግር አጥበዋል።

ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሊቀ ጻጻሳት ዘካቶሊካውያን፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ዝቅ ብሎ የፍጡራንን እግር በማጠብ ትህትናውን እንዳስተማረን ክርስቲያኖች ይህንኑ ምግባር ተከትለው እርስ በእርስ መከባበር ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ምዕመናንም በዓሉን ሲያክብሩም ሆነ በሌላ እለት ተእለት ኑሯቸው ከክርስቶስ በወሰዱት አርአያነት ለሰዎች በጎ በመሆን እና ትህትናን መተግበርን ማሰብ እና መተገበር እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡

የፀሎተ ሐሙስ በዓል በርካታት ትርጉሞች ያሉት የተናገሩት በኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ ስራ አስኪያጅ ዶክተርር አባ ኃይለ ማርያም፥ ከሃይማኖታዊ ትርጉም ባሻገር ማህበራዊ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል፡፡

በነገው እለት ምእመና በየአብያተ ክርስቲያናት ተሰብስበው በጾም፣በጸሎት፣ በስግድትና በምስጋና ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ሲል የተቀበለውን መከራ እያሰቡ የስቅለት በዓልን ያከብራሉ።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy