Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

መልካም አስተዳደር የዴሞክራሲ መሠረት

0 1,470

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

መልካም አስተዳደር የዴሞክራሲ መሠረት …/ወንድይራድ ኃብተየስ/

መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ባህል ግንባታን በግብነት አስቀምጦ መረባረብ ወሣኝ ጉዳይ ይሆናል። ታዲያ ይህን እውነታ በውል በመገንዘብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሃሳቡን ወደ ድርጊት ለመለወጥ በጥረት የታገዙ ጠንካራ እንቅስቃሴዎች ከተጀመሩ ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል።

እስቲ በቅድሚያ ስለ መልካም አስተዳደር የሂደት ግንባታ ጥቂት እንበል። በዓለም ባንክ ብያኔ መሠረት መልካም አስተዳደር ማለት ሊተነበይ የሚችልና በነጠረ ፖሊሲ አወጣጥ የተካነ እንዲሁም በሙያው ሥነ ምግባር የሚታገዝና በሚወስዳቸው ርምጃዎች ተጠያቂ ሊሆን የሚችል መንግሥትና በመንግሥታዊ ጉዳዮችም በንቃት የሚሳተፍ ኅብረተሰብ ያለበት ሆኖ ሁሉም አካላት በህግ የበላይነት አምነው የሚንቀሳቀሱበት ሥርዓት ነው።

እርግጥ በዚህ ትርጓሜ ውስጥ ያሉት አባባሎች ለመልካም አስተዳደር ጠቃሚ መሆናቸው አያጠያይቅም። ይሁን እንጂ አባባሎቹ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታቸውን ከዛሬ ሁለት መቶ ዓመታት በፊት መሥርተው በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሰዋል በሚባሉት ምዕራባውያን እንኳን ሙሉ ለሙሉ ገቢራዊ ሆኗል ብሎ ለመናገር አያስደፍርም። ከኢትዮጵያ የ25 ዓመታት ታዳጊ ዴሞክራሲ አንጻር ተግባሩ ተቃዋሚዎች “መንግሥት ባለፉት ዓመታት መልካም አስተዳደርን አላሰፈነም” እያሉ እንደሚያስወሩት ሳይሆን የራሱን ሂደት ጠብቆ በጊዜ ዑደት ውስጥ የሚገነባ ሆኖ እናገኘዋለን።

ከመልካም አስተዳደር አኳያ በመጀመሪያ መታወቅ ያለበት ጉዳይ ተግባሩ በሂደት እንጂ በአንድ ጀምበር የሚመጣ አለመሆኑን ነው። ምዕራባውያንም ቢሆኑ ዛሬ ለደረሱበት የመልካም አስተዳደር ተግባር ለዚያውም ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ባላደረጉበት ሁኔታ ረጅም ጊዜ የወሰደባቸው መሆኑን መገንዘብ ያሻል። በመሆኑም እንደ ኢትዮጵያ ያለ ጀማሪ የዴሞራሲያዊ ሥርዓት ባህል ግንባታ አራማጅ አገር ተግባሩን ‘በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ካላመጣች’ ብሎ በጭፍን መሞገት ግራ የሚያጋባ ነው።

መልካም አስተዳደርን ማስፈን የኪራይ ሰብሳቢነትን አንድ መንገድ መዝጋትና የአገሪቱን ልማት ማፋጠን ነው። በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት ለመልካም አስተዳደር መስፈን የተለያዩ ርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል። ሆኖም ግን መልካም አስተዳደርን የማስፈን ተግባር የአንድ ጀምበር ተግባር አይደለም። ጊዜን የሚጠይቅና በሂደቶች የሚከወን እንደሆነ ይታወቃል።

በአገሪቱ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዕድገት የሚወሰነውንና በየጊዜው መሻሻል እያሳየ የሚገኘውን የመልካም አስተዳደር ክንዋኔን በአንድ ለሊት እንዲጠናቀቅ የሚፈልጉ አንዳንድ ወገኖች መልካም አስተዳደር የለም እያሉ በተደጋጋሚ ከማስተጋባት ባሻገር በየጊዜው የተለያዩ ፀረ ዴሞክራሲያዊ እሳቤዎችን በማምጣትና በአገሪቱ የተረጋገጠውን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በማያግዝና ለማጠናከር በማይጠቅም መልክ ሲንቀሳቀሱ ይስተዋላል።  

በኒዩ ሊበራል እሳቤ ውስጥ ሰምጠው ከወዲያ ወዲህ የሚላጉት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ‘መንግሥት መልካም አስተዳደርን ማስፈን ተስኖታል’ እያሉ የሚያላዝኑት የአላዋቂነት ተረት ተረት በጥልቀት መፈተሽ ይኖርበታል። ተግባሩን ከሰማይ በአንድ ቀን እንሚወርድ መና ቆጥረው ‘የግድ አሁኑኑ መፈፀም አለበት’ ብሎ ማሰብ ከእውቀት አጠርነት በስተቀር ሌላ ሥያሜ አያሰጥም።

ይሁንና መንግሥትና ገዥው ፖርቲ መልካም አስተዳደር ጊዜ ስለሚወስድ ተግባሩን ላለማከናወን እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጥ አላሉም። ይልቁንም ላለፉት 26 ዓመታት መልካም አስተዳደር በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ባህል ግንባታ ውስጥ ሥር እንዲሰድ ዘርፈ ብዙ ጥረት አድርገዋል።

በዚህ አገር ባለፉት  ዓመታት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል፤ አጥጋቢ ውጤቶችም ተገኝተዋል። የአገራችን ዴሞክራሲ ሥር መስደድ ይችል ዘንድ በሁሉም ደረጃዎች የዴሞክራሲ ተቋማት እንዲቋቋሙና እንዲጠናከሩ፣ የዳበረ የፍትህ ሥርዓት እንዲገነባ፣ የህዝቡ ዴሞክራሲያዊ ባህል እንዲጎለብት፣ በየደረጃው ባሉ የመንግሥት አካላት ውስጥ የግልፅነት፣ የተጠያቂነትና የህዝብ አገልጋይነት መርህ እንዲሰፍንና የተግባር መመሪያ እንዲሆን ብሎም በሁሉም መስኮች የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ…ወዘተ ብርቱ ጥረት ተደርጓል። ወደፊትም ይኸው ይቀጥላል።

መንግሥት በአገሪቱ መልካም አስተዳደርን የማስፈን ተግባር ልማታዊ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከሚኖረው ሚናና የህዝብን ጥያቄ ከመመለስ አንጻር ቀዳሚ አጀንዳው

አድርጎ የያዘው ጉዳይ ነው። መልካም አስተዳደር የህልውና ጉዳይ ነው። ምክንያቱም መልካም አስተዳደርን ማስፈን ካልተቻላ ኪራይ ሰብሳቢነትን ደፍቆ ልማታዊነትን ማረጋገጥ የራሱ አሉታዊ ተጽዕኖ ስላለው። የመልካም አስተዳደር ትግበራ የአገራችንን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እለታዊ ህይወት በቀጥታ የሚነካ በመሆኑ፤ በአተገባበሩ ዙሪያ ከአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ አኳያ መጠነ ሰፊ ተግባራዊ ክንዋኔዎች ተደርገው አበረታች ለውጦች እየተመዘገቡ መጥተዋል።

የሆነ ሆኖ ኢሕአዴግ ውስጡን በማጥራት የህዝብን ቅሬታዎች ለመፍታትና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠል ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም። ኢሕአዴግ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመተባበር እስካሁን ድረስ የተገኘውን የሠላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ስኬቶችን በማጠናከርና  መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የተጀመሩ ጥረቶችን የበለጠ በማጎልበት በቁርጠኝነት መሥራት የግድ ይለዋል።

ባለፉት ወራት በየመድረኩ ከኅብረተሰቡ ጋር በመሆን በተደረጉ ውይይቶች በርካታ ከአገልግሎት ተደራሽነትም ሆነ ከአፈጻፀም ጉድለት ጋር የሚነሱ ቅሬታዎች እንዳሉና ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግም ይህንን ከግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለበት ተጠቋቁሟል።

ኢሕአዴግ ውስጡን በማጥራት የህዝብን ቅሬታዎች ለመፍታትና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠል ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም።  መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመተባበር እስካሁን ድረስ የተገኘውን የሠላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ስኬቶችን በማጠናከርና  መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የተጀመሩ ጥረቶችን የበለጠ በማጎልበት በቁርጠኝነት መሥራት የግድ ይላል። በየመድረኩ ከኅብረተሰቡ ጋር በመሆን በተደረጉት ውይይቶች በርካታ ከአገልግሎት ተደራሽነትም ሆነ ከአፈጻጸም ጉድለት ጋር የሚነሱ ቅሬታዎች እንዳሉና ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ይህንን ከግምት ማስገባት እንዳለበት ተጠቋቁሟል።

እነዚህ ቅሬታዎች በዝርዝር የተለዩ በመሆናቸው ጊዜ ሳይሰጡ ከህዝቡ ጋር በመሆን ለመፍታትና ለወደፊቱም እያደጉ የሚሄዱ ፍላጎቶችን ለማርካት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እንደሚታገሉ  በተለይም ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን አምርረው በመታገል ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ያለው አሠራር በማጎልበት የታዩ ጉድሎቶችና የህዝብ ቅሬታዎች በሚገባ መረባረብ የግድ ይላል።  

ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋትና ልማታዊነትን ለማጠናከር መልካም አስተዳደር ማስፈን ቀዳሚው ተግባር ነው። እንደ መሬት፣ የመንግሥት ግዥ፣ ግብርና ንግድ የመሳሰሉ ለኪራይ ሰብሳቢነት ዋና ምንጭ ተደርገው የሚወሰዱ ዘርፎች ተለይተው ታውቀዋል።

የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ መሠረት በመናድ የልማታዊ ኢኮኖሚን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ሁለንተናዊ ጥረት ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል። ልማታዊነት ተረጋግጦ ኪራይ ሰብሳቢነትን ነቅሎ ለመጣል ትንቅንቁ ተጀምሯል። በተመሳሳይ መልኩ የኪራይ ሰብሳቢነትን የበላይነት ለመድፈቅና ልማታዊነትን ለማንገስ ቀላል የማይባል ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።

ኢሕአዴግ ቀጣይ ዋና አጀንዳው መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመድፈቅ የሚያስችል ሥራ አጠናክሮ መከወን እንደሆነ በተለያየ ጊዜ ተገልጿል። ለዚህ ተግባራዊነትም ኅብረተሰቡ ጠንክሮ ሊተባበር ይገባል። መልካም አስተዳደር የዴሞክራሲ አካልና መሠረት ነውና።

…/ወንድይራድ ኃብተየስ /

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy