Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በሎሚና ጨው የራስ ምታት ህመምን ለማከም

0 14,567

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በሎሚና ጨው የራስ ምታት ህመምን ለማከም…

ከባድ የራስ ምታት ህመም (ማይግሬን) በአለማችን የበርካቶች ስጋት መሆኑ ይነገራል።

ጭንቀት፣ አደንዛዥ እፆችን መጠቀም፣ የምግብ እጥረት፣ የሆርሞን አለመመጣጠን እና የመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት ለህመሙ በመነሻነት ይጠቀሳሉ።

አዕምሯችን ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ የደም ስሮች መካከል ተለቅ የሚሉት ሲያብጡና ሲሰፉ ነው ህመሙ የሚከሰተው።
የእነዚህ የደም ስሮች እብጠት በዙሪያቸው ከሚገኙ ነርቮች የተለያዩ ንጥረ ነገሮች እንዲለቁ ያደርጋል፡፡

በሌላ መልኩ ደግሞ እነዚህ የተመረቱ ንጥረ ነገሮች አዕምሮአችን ለህመም ያለውን ስሜት ከፍ ያደርጉታል፡፡
ከፍተኛ የሆነ በተደጋጋሚ የሚነሳ እና በመሃል እረፍት የሚሰጥ አይነት የራስ ምታት የመጀመሪያው የማይግሬን ምልክት ነው፡

ህመሙ ቀስ በቀስ የሚጨምር ሲሆን ከእንቅልፍ ስንነሳ ህመሙ የሚበረታ ከሆነ ግን ከፍተኛው የህመም ደረጃ ላይ መድረሱን ያመላክታል። ማይግሬን ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ በየቀኑ መድሃኒት መውሰድ ግድ ሊሆን ይችላል።

ህመሙ እዚህ ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊትም ሆነ የህመሙን ስሜት ለመቀነስ ግን የሚከተለውን አመራጭ መጠቀም የላቀ መፍትሄ ያስገኛል ነው የሚለው የሄልዚ ላይፍ ላንድ ድረ ገጽ ዘገባ።
ለዚህም የሚያስፈልጉት የተፈጨ ጨው፣ የሎሚ ጨማቂ እና የሎሚ ቅርፊት ናቸው ብሏል።
ጨው ጭንቀትን በማስወገድ ደስታ እንዲሰማን የሚያደርገውን ሴሮቶኒን የተሰኘ ሆርሞን መመረትን ይጨምራል።
ጭንቀት ለከባድ የራስ ምታት ህመም (ማይግሬን) መነሻ መሆኑን ተከትሎም አንዳንድ ሰዎች በአፋቸው ውስጥ ጨው መያዝን ከህመሙ ለመገላገል ይጠቀሙበታል።

የሁለት ሎሚ ጭማቂ፣ የተፈጨ የሎሚ ቅርፊት ከሁለት ማንኪያ ጨው ጋር ካደባለቅን በኃላ በቀዝቃዛ ስፍራ ማስቀመጥና ከዚያም ከተወሰነ ውሃ ጋር ቀላቅለን መጠጣት ከህመሙ ለማገገም ይረዳል ተብሏል።ምንም እንኳን ውህዱ መራራ ቢሆንም ህመሙ ከሚያደርሰው ጉዳት አይበልጥምና ይሞክሩት ይላል ድረ ገጹ፡፡
ይሁን እንጂ ከፍተኛ የደም ግፊት ህመም ካለብዎ ጨው ችግሩን ስለሚያባብሰው ከላይ የጠቀስነውን ውህድ ባይጠቀሙት ይመከራል።
ምንጭ ፡ የሄልዚ ላይፍ ላንድ ድረ ገጽ ዘገባ።

ሚያዝያ 26/2009 ዓ.ም ከባድ የራስ ምታት ህመም (ማይግሬን) በአለማችን የበርካቶች ስጋት መሆኑ ይነገራል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy