Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተናዎች ላይ ኩረጃ እንዳይፈፀም እየተሰራ ነው

0 2,264

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

) ዘንድሮ በሚካሄዱ የመሰናዶና የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተናዎች ላይ የኩረጃ ድርጊት እንዳይፈጸም ልዩ ዝግጅት መደረጉን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ገልፀዋል።

የመሰናዶና የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ተፈታኞች፥ የመግቢያ ፈተናውን ለመውሰድ ልዩ ዝግጅት ማድረጋቸውን ይናገራሉ።

ፈተናው የዓመታት ጥረታቸውን ውጤት የሚያዩበትና ወደ ሚፈልጉት የህይወት ጎዳና የሚያመሩበት መንገድ በመሆኑ በጥንቃቄ መዘጋጀታቸውንም ነው የሚናገሩት።

ተማሪዎችቹ የፈተና ዝግጅታቸውን በቡድንና በተናጠል በመሆን ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ ተማሪዎች ፈተናውን በራሳቸው አቅም ለመስራት መዘጋጀታቸውን ጠቁመው፥ ሌሎች በቂ ዝግጅት ያላደረጉ ተማሪዎች ኩረጃን ለመፈጸም ዝግጅት እንደሚያደርጉም ይጠቁማሉ።

ይህ ዓይነቱ ተግባር ደግሞ ከስነ ምግባር ውጭ የሆነና ለማንም የማይጠቅም ድርጊት ነው ይላሉ ተማሪዎቹ፡፡

የዳግማዊ ሚኒሊክ መሰናዶ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ተገኔ መንግስቱ እንደሚገልጹት፥ ኩረጃን ለመከላከል በተማሪዎቹ ቀጣይ ህይወት ላይ የሚኖረውን አሉታዊ ተጽእኖ እንዲረዱና ድርጊቱን እንዲጸየፉት የሚያደርግ ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ በትምህርት ቤቱ ተሰርቷል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም በተለያዩ የመሰናዶና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባደረገው ቅኝት፥ ኩረጃን የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን ታዝቧል።

በየዓመቱ ለመሰናዶ እና ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የሚዘጋጁ ፈተናዎች ተማሪዎች በየክፍል ደረጃቸዉ ማወቅ የሚገባቸውን እውቀትና ክህሎት በመፈተሽ ብቁ የሆኑትን ብቁ ካልሆኑት የሚለይባቸው መሳሪያዎች ናቸው።

በመሆኑም የፈተናው ሂደት ከኩረጃ በፀዳ መልኩ ካልተከናወነ በሀገሪቱ እድገት ላይ የሚያመጣው ኪሳራ ዘርፈ ብዙ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ተክለ ማርያም ይገልጻሉ።

ይሁን እንጂ ኩረጃን መከላከልና ከኩረጃ የፀዳ ምዘናን ማካሄድ ተማሪዎች በራስ መተማመን የትምህርት ምዘናዎችን እንዲሰሩ ለማድረግ የሚያስችሉ የስነ ልቦና ዝግጅቶች ከታችኛው የክፍል ደረጃ ጀምሮ መገንባትን ይጠይቃል።

ለዚህም ተከታታይ የምዘና ስርዓትን በመተግበር ከታችኛው ክፍል ጀምሮ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ ይናገራሉ።

የሀገር አቀፉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርዓያ ገብረእግዚያብሄር በበኩላቸው፥ የፈተና ኩረጃን መቅረፍ ካልተቻለ እንደሀገር የሚፈለገውን ፈጣን እድገት ማሳካት አይቻልም ብለዋል።

የፈተና አስተዳደርና ቁጥጥሩን ማጥበቅና ዘመናዊ የሆኑ የፈተና ዝግጅትና የአፈታተን ስልቶችን ጥቅም ላይ ማዋልም ሌላኛው የችግሩ መከላከያ መንገድ በመሆኑ፥ ኤጀንሲው በዚህ ዓመት ለሚካሄደው ፈተና በተለየ ሁኔታ ዝግጅት ማድረጉን አቶ አርዓያ ገልጸዋል።

በዘንድሮው ዓመትም 288 ሺህ 626 የ12ኛ ክፍል፣ 1 ሚሊየን 206 ሺህ 839 የ10ኛ ክፍል ተፈታኞች ብሔራዊ ፈተና ይወስዳሉ።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy