Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እየተመዘበረች መሆኑ ተገለጸ

0 772

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አፍሪካ በየዓመቱ በበሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ እንደምትዘረፍ የብሪታኒያ እና የአፍሪካ ባለሙያዎችን ጥናትን ዋቢ በማድረግ  ዘጋርዲያን ዘገበ፡፡

እንደ ጥናቱ ከሆነ ከአፍሪካውያን ይልቅ  የተቀረው ዓለም ከአፍሪካ ሀብት ተጠቃሚ ነው፡፡

እ.አ.አ በ2015 162 ቢሊዮን ዶላር በእርዳታ እና ብድር አፍሪካ ስትቀበል በተመሳሳይ ዓመት 203 ቢሊዮን ዶላር አህጉሪቱ ተመዝብራለች፡፡

አህጉሪቱ የሚታየው የህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር 68 ቢሊዮን ዶላር በዓመት ይደረሳል፣ ይህም አህጉሪቱ በዓመት ከምታገኘው የ19 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ የበዛ ነው፡፡

የዚህ ሁሉ የገንዘብ ቀውስ ምክንያየቱ ፍትዓዊ የብድር አከፋፈል አለመኖር፣ የውጭ ድርጅቶች የግብር መደበቅ ዝንባሌ እና ሙስና መሆናቸው በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

እ.አ.አ በ2015 አፍሪካ 32 ቢሊዮን ዶላር የተበደረች ሲሆን በዛው ዓመት 18 ቢሊዮን ዶላር ለብድር ወለድ ብቻ ከፍላለች፡፡ ይህም የብድር ወለዱ አፍሪካን ምን ያህል እየበዘበዛት እንደሚገኝ ያሳያል ፡፡

በመሆኑም ወደ አፍሪካ የሚገቡ ኢንቨስትመንቶች በግብር ገነት ውስጥ መኖራቸው አስፈላጊ አለመሆኑን ጥናቱ ይመክራል፡፡ ወደ አህጉሪቱ የሚገቡ ብድር እና ድጋፎችም ተልዕኳቸው ሊታወቅ ይገባል እንደ ጥናቱ ማብራሪያ፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy