Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ አደጋን ተቋቋሞ እድገቱን መቀጠል የሚችል ኢኮኖሚ ገንብታለች – ብሔራዊ ባንክ

0 705

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ አደጋን ተቋቋሙ እድገቱን መቀጠል የሚችል ኢኮኖሚ መገንባቷን የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ ዶክተር ዮሐንስ አያሌው ተናገሩ።

ምክትል ገዢው ዶክተር ዩሃንስ አያለው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ ሀገሪቱ ባለፉት 26 ዓመታት ያስመዘገበችው እድገት የዜጎችን የነፍስ ወከፍ ገቢ እጅጉን ማሳደግ የቻለ ነው ብለዋል።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ ርሃብ የኢትዮጵያ መታወቂያ በነበረባቸው ዓመታት የኑሮ ውድነቱ በየዓመቱ እየናረ በአማካይ ዘጠኝ በመቶ ይጨምር ነበር።

ይህ መሆኑ ደግሞ በወቅቱ የኢትዮጵያውያን የነፍስ ወከፍ ገቢ በትክክለኛ መመዘኛው በየዓመቱ በሁለት በመቶ ገደማ እንዲቀንስ አድርጎታል፡፡

ስለዚህ ሀገሪቱ ወደ መልካም የኢኮኖሚ ጉዞ ለመንደደር ባላት አቅም ማተኮሯ ዜጎችን ሙሉ በሙሉ በበቂ ሁኔታ መመገብ ባይቻል እንኳ ተጨማሪ ርሃብ እንዳይኖር መንገድን ለመክፈት ያግዛል ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዥ እና ቺፍ ኢኮኖሚስት ዶክተር ዮሀንስ አያሌው እንደሚሉት ኢትዮጵያ በ1983 ዓ.ም ከእዝ ስርዓት ወጥታ የገበያ ኢኮኖሚን መከተል ስትጀምር እስከ ቀጣዮቹ አስርት ዓመታት እንኳ ወደ እድገት ለመምጣት አስቸጋሪ የሆኑ ጊዜያትን አልፋለች ፡፡

ዶክተር ዮሐንስ ከ1983 እስከ 1993 ዓ.ም ባሉት 10 ዓመታት ሀገሪቱ ኢኮኖዋሚን በማረጋጋት ላይ አተኩራ ነበር ብለዋል፡፡

ከ1994 ዓ.ም ወዲህ ግን ኢኮኖሚውን በአንድ መልኩ ከሌሎች ሀገራት በሌላ በኩል ደግሞ ከሀገሪቱ ነባራዊ የልማት ፖሊስ የተቀዳ መርህ እንዲመራው ተደርጓል፡፡

ሀገሪቱ ካለፉት 14 ዓመታት ወዲህ ባለሁለት አሃዝ እድገትን ይዛ በአጠቃላይ የምታመርተው ምርት ወይም ባለሙያዎቹ ጂዲፒ የሚሉት አሁን ላይ 400 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡

በኢትዮጵያ ምድር ብቻ በዓመት የተመረቱ ምርቶች ዋጋቸው 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ዋጋን ማውጣት ጀምረዋል ።

100 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚረዝም አስፋልት መንገድ ተሰርቶ ዜጎችን እና ምርቶችን በፍጥነት ማጓጓዝ የሚቻልበት ላይ ሲደረስ፥ ቀድሞ በ10 ሚሊዮን ኩንታል ብቻ ሰብል ሲመረት ከነበረበት ማሳ ላይ አሁን በ100 ሚሊዮኖች ኩንታል ምርት ማግኘት ተችሏል፡፡

ሀገሪቱ ባለፉት 14 ዓመታት ውስጥ ራሱን በሁለት እጥፍ ያሳደገ ኢኮኖሚ ላይ እንድትደርስ ከቱሪስት መስህብ ከ3 ነጥብ 2 ቢሊየን አሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ስታገኝ፥ የውጭ ሀገር ባለሃብቶች በግማሽ ዓመት ውስጥ ብቻ 2 ቢሊየን ዶላር ፈሰስ ማድረጋቸውም ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡

ባለንበት ወቅት ኢትዮጵያውያን በየዓመቱ ካላቸው 100 ብር ላይ ዘጠኝ ብር በነፍስ ወከፍ ጭማሪ ማሳየቱ የኢኮኖሚ ስሪቱ ውጤት ነው ይላሉ ዶክተር ዮሀንስ፡፡

በስትራትሊንክ አፍሪካ አጥኚና ተንታኝ የሆኑት ጁሊያንስ አምቦኮ፥ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ የአፍሪካን መነቃቃት ማሳያ ናት ብለዋል ።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሃምሳ ዓመት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ድርቅ አጋጥሟት የግብርናዋን እድገት ወደ ታች ቢጎትተውም ኢንዱስትሪዋ 20 በመቶ አድጓል፡፡

ዶክተር ዮሃንስ አሁን ላይም የሚያጋጥሟትን ችግሮች ተቋቁማ የስምንት በመቶ እድገት ማሳየቷ ካላት አቅም ላይ ተጨማሪ አቅምን የመጨመር ውጤት ነው ብለዋል ።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy