Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የባቡር ግንባታው ዘርፍ እመርታ እንዲጠናከር

0 944

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የባቡር ግንባታው ዘርፍ እመርታ እንዲጠናከር…

                                                      ቶሎሳ ኡርጌሳ

ባቡር ለአንድ ሀገር ምጣኔ ሃብታዊ እመርታ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው። የየብስ ጉዞን የሚያሳልጥና ከሀገራችን  ዘርፍ ነው። የዘርፉ ግንባታ ለዜጎች ስራ ፈጠራ ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ሲሆን፤ ለሀገር አጠቃላይ ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት ብሎም ከጎረቤት ሀገራት ጋር ለሚደረገው የንግድ ልውውጥ ጉልህ ሚና ይጫወታል።  

በመሆኑም ይህን ተግባር እንዲወጣ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 141/2000 በህዳር ወር 2000 ዓ.ም የመንግስት የልማት ድርጅት ሆኖ በአዲስ መልክ እንዲቋቋም ተደርጓል። የኮርፖሬሽኑ ዋና ዓላማ ተፎካካሪና አቅምን ያገናዘበ የትራንስፖርት አገልግሎት ማረጋገጥ የሚችል የተቀናጀና ከፍተኛ አቅም ያለው የባቡር ትራንስፖርት ስርዓት መዘርጋት መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

መንግስት እያከናወነ ካለው የባቡር መስመር ዝርጋታ አቅጣጫ አኳያ የባቡር መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ነድፎ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ነው። በዚህም መሰረት በተለያዩ አቅጣጫዎች የተያዙ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን አቅም በፈቀደ መጠን ጥረት እየተደረገ ነው። በተለይም ከፕሮጀክቶቹ መካከል ለወጪ ንግዳችን ቁልፍ እንደሚሆን የሚጠበቀውን መስመር በማከናወን ሀገሪቱ ከጎረቤት ሀገሮች ጋር ያላትን የየብስ ግንኙነት ለማጠናከር እየሰራ ይገኛል። በተለይም በአሁኑ ወቅት ከሰበታ እስከ ጂቡቲ ድረስ የተዘረጋውና ግንባታው ተመርቆ የሙከራ ተግባር በማካሄድ ላይ የሚገኘው የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መስመር በዚህ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

እንደሚታወቀው ቆጣቢ የሆነ የየብስ ትራንስፖርት ስርዓት ለማካሄድ የባቡር መስመር ተመራጭ ነው። ይሁንና የባቡር መስመር አዋጭ የሚሆነው ከፍተኛ ጭነት ወይም መንገደኛ ባለበት እንጂ ውስን ተጓዥ ወይም ጭነትን በማጓጓዝ ረገድ ይህን ያህል አዋጭ እንደማይሆን በዘርፉ የተሰማሩ ሁራን ይገልፃሉ።

ነገር ግን የምጣኔ ሃብት እድገታችን በተፋጠነ ልክ፤ ይኸው ፍጥነት ከዚህ በበለጠ እንዲቀጥል ቀልጣፋና በዋጋ ተወዳዳሪ የሆነ የየብስ ትራንስፖት አገልግሎት እንደሚያስፈልገን ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው። ርግጥ ሀገራችን ልትጠቀምባቸው ከምትችለው ዋና ዋና ወደቦች ጋር የሚያገናኝ የባቡር መስመር ያስፈልገናል። በሀገር ውስጥም ዋነኛ የትራስፖርት ኮሪደሮችን የሚያገናኝ የባቡር መስመር እንደሚያስፈልገን እንዲሁ።

እንደሚታወቀው ቀደም ባሉት ጊዜያት ለባቡር ትራንስፖርት በቂ ትኩረት ስላልተሰጠውና የሚፈልገውም ወጪ እጅግ በጣም ከፍተኛ ስለሆነ ፋይዳ ያለው የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትን ሳንጠቀም ዛሬ ላይ ደርሰናል። ይሁንና መንግስት ይህንን ሁኔታ ለመቀየር አቅም በፈቀደ መጠን በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። አሁን በምንገኝበት ተጨባጭ ሁኔታ የመንገድና የባቡር ትራንስፖርትን በማቀናጀት ፈጣን እንዲሁም በዋጋ ተወዳዳሪ የሆነ የትራንስፖርት ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባን ግልፅ ነው። ይህን ነባራዊ ሁኔታ በሚገባ የሚረዳው የኢፌዴሪ መንግስትም ፈጣንና ቀጣይነት ያለውን ልማት የበለጠ ማረጋገጥ የሚያስችለውን የየብስ ትራንስፖርት ስርዓት ገንብቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

የቀላል ባቡር ፕሮጀክቱ በኤሌትሪክ የሚሰራ በመሆኑ ሀገራችን ለነዳጅ ታወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ ለመቆጠብ እንዲሁም የአየር ብክለትን በመከላከል ረገድ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው። የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማሳለጥ በኩልም ጠቀሜታው የላቀ ነው። በዚህም ሀገሪቱ በቀጣይ ለምታከናውናቸው መሰል ግንባታዎች የሀገራችን ሰራተኞች የሚቀስሙትን ዕውቀት ተጠቅመው ሙሉ በሙሉ የመስራት ችሎታቸውን ሊያዳብሩ ይችላሉ።

ታዲያ እዚህ ላይ የባቡር መስመር ዝርጋታ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ከማረጋገጥ አኳያ የላቀ ሚና ይጫወታል ሲባል፤ ሽግግሩ ሀገራችን ለወጠነቻቸው የልማት ፕሮግራሞች ማሳኪያ ምን ዓይነት ቴክኖሎጂ እንደሚያስፈልጋት ለይቶ መጠቀም ወሳኝ መሆኑ አያጠያይቅም። እናም በቅድሚያ በሂደት መቅዳት፣ መላመድና ማሻሻል በስተመጨረሻም ቴክኖሎጂውን በማመንጨት የሚጠበቁ ተግባራት መሆናቸውን ልብ ማለት ይገባል፡፡

ርግጥ የሌሎች ሀገሮች ተሞክሮ ለመረዳት እንደሚቻለው የጎንዮሽና የቀጥታ የቴክኖሎጂ ማሸጋገርያ መንገዶች አሉ፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያን በመሰሉ በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ሊከተሉት የሚገባው አካሄድ፤ ፈጣን የምጣኔ ሃብት ዕድገት ካስመዘገቡት ሀገራት ልምድ በመቅሰም የሚከናወነው የልማት ስራ የተሻለ ውጤት ያስገኛል። እናም ፈጣን ለውጥ ለማምጣት መሰረታዊ የሚባለው የጎንዮሽ የቴክኖሎጂ ሽግግር በብዙ መንገዶች ሊገኝ ይችላል። የባቡር ዝርጋታ ፕሮጀክት ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ሲሄድ የሀገሪቱ ባለሙያዎች ትምህርት መቅሰማቸው አይቀሬ ነው። ለወደፊቱም መሰል ፕሮጀክቶች በሀገራችን ሲገነቡ በእኛው መሃንዲሶች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚደረጉ ይታመናል።

ስለሆነም ሀገራችን ላለፉት 15 ዓመታት በተከታታይ ያስመዘገበችው ከአስር በመቶ በላይ አማካይ የምጣኔ ሃብት ዕድገት ሀገሪቱ በ2025 ልትደርስበት ያሰበችውን የመካከለኛ ገቢ ጎራ ካላቸው ሀገራት የመቀላቀል ዕድልን መደላድል እንደሚፈጥር ጥርጥር የሚኖረው አይመስለኝም። በተለይም የሀገራችንን ከተሞች፣ ክልሎችንና አጎራባች ሀገሮችን የሚያስተሳስሩ መሰረተ ልማቶች ለዚህ ዕቅድ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ናቸው።

በአሁኑ ወቅት በኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ በቴሌኮም፣ በመንገድ እና በባቡር መስመር ዝርጋታ እየተደረጉ ያሉ ሰፊ መሰረት ያላቸው የልማት ፕሮጀክቶች በተገቢው መንገድ በመከናወን ላይ ይገኛሉ። በተለይም በትራንስፖርት ዘርፍ በኩል የባቡር አገልግሎት በፍጥነት ግዙፍ የሆነን ሎጀስቲክካዊ አቅርቦት ወደ ተፈለገበት ቦታ ስለሚያደርስ አገልግሎቱ የአማራጮች ሁሉ ቅድሚያ መሆኑ የሚካድ አይደለም። መንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ የባቡር መስመር ዝርጋታውን በማሳለጥ ላይ የሚገኘውም ለዚሁ ነው።

እንደሚታወቀው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚዘረጉ የባቡር መስመሮች በመጀመሪያው ምዕራፍ ከተካተቱ ውስጥ የአዲስ አበባ- ድሬዳዋ- ደዋሌ ፕሮጀክት አንደኛው ሲሆን፤ የስድስት መቶ ሃምሳ ስድስት ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ነው። ፕሮጀክቱ ከሃምሳ አምስት በላይ ጣቢያዎችም ይኖሩታል። የአዋሽ- ወልዲያ- መቀሌ ፕሮጀክት ደግሞ አምስት መቶ ሃምሳ ስድስት ነጥብ ሁለት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን፤ ከሃያ ሶስት በላይ ጣቢያዎች የሚኖሩት ነው።

ይህ ፕሮጀክት ሀገራችንን ከጎረቤት ጁቡቲ ጋር በማገናኘት ለመካከለኛው ኢትዮጵያ የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል። ዝርጋታው ሲጠናቀቅም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግዙፍ የሆኑ ሎጀስቲካዊ አገልግሎቶችን በፍጥነት ለመለዋወጥ ያስችላል።

ይህ ሲሆንም ግዙፍ የሆኑ ሎጀስቲካዊ ዕቃዎች በሁለቱም ሀገራት በፈጣን ጊዜ መከናወናቸው ደግሞ፤ አንድም ጊዜን ከመቆጠብ፣ ሁለትም የባቡር መስመር ዝርጋታው ዘመኑ በሚጠይቀው የኤሌትሪክ ሃይል ስለሚንቀሳቀስ ሀገራቱ ለነዳጅ ያወጡት የነበረውን ከፍተኛ ወጪ ይቀንሳል። ሌላኛው ፕሮጀክት ደግሞ የሰሜኑን የሀገራችን ክፍል ከመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍል ጋር የሚያገናኝ ነው። ፕሮጀክቱ የወልድያ- ሰመራ- ገላፊ ገበያ የምድር ባቡር ፕሮጀክት ይሰኛል። ይህ መስመር ሁለት መቶ ሃምሳ ስድስት ነጥብ አራት ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፤ ከሃያ አምስት በላይ ጣቢያዎች ይኖሩታል ተብሎ ይጠበቃል።

ሌላኛው የአዲስ አበባ -ኢጂጆ- ጅማ- በድሪ ፕሮጀክትም ሶስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ነጥብ ሶስት ኪሎ ሜትር ርዝመት ነው። በሃያ አምስት ጣቢያዎች አገልግሎት እንዲሰጥ ተገርጎም የሚገነባ ነው። ኢትዮጵያን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያገናኝ ያገናኛል። ከጆሞ- ኮንሶ የሚዘረጋው ባለ አምስት መቶ ሰማንያ ሰባት ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ዝርጋታ ደግሞ ሀገራችንን ከኬንያ ጋር የሚያገናኝ ፕሮጀክት ነው። ከአዋሽ – ኮምቦልቻ – ሃራ ገበያ የምድር ባቡር መስመር ግንባታ ፕሮጀክትም ተጠቃሽ መስመር ነው። ይህ ፕሮጀክት እንደ ሌሎች ፕሮጀክቶች ሁሉ የኤሌትሪክ ኃይል ይጠቀማል ተብሎ በዕቅድ የተያዘ  ሲሆን፤ ሶስት መቶ ሰባ አምስት ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ይኖረዋል። የሚሰጠው አገልግሎቱም ለጭነትና ለመንገደኞች ማመላለሻነት ነው።

ታዲያ እዚህ ላይ የባቡር ግንባታ መስመሮቹ ግንባታ ሁለት ጠቀሜታ እንዳላቸው መገንዘብ ይገባል—በሀገር ውስጥና በውጭ። በሀገር ውስጥ ምርትና መንገደኞችን በተቀላጠፈ ሁኔታ በማቀራረብ የንግድ ልውውጡን ያሳልጣሉ። እንዲሁም የዜጎችን ህይወት ቀላል ያደርጋሉ። ከውጭ አኳያም የሀገራችንን ወጪና ገቢ ምርቶችን በተሻለ ፍጥነት ለማስወጣትና ለማስገባት በጉዞ ላይ ይባክን የነበረውን ጊዜ ይቆጥባሉ። ኢትዮጵያ ከዘርፉ የምታገኘውን ጥቅምና አቅምንም ያሳድጋሉ። ሀገሪቱን ከጎረቤቿ ጋር በማገናኘትም የሚኖረውን የሁለትዮሽ ምጣኔ ሃብታዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት በእጅጉ እንዲጠናከሩና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ እንዲጎለብት ያደርጋሉ። እናም የባቡር ግንባታው ዘርፍ እመርታ ይጎለብት ዘንድ የባለ ድርሻ አካላትም ይሁን የዜጎች ተሳትፎ ሊደረጅና ሊጎለብት ይገባል እላለሁ።  

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy