የፖላንድ ፕሬዚዳንት አንድሬ ዱዳ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው።
ፕሬዚዳንቱ ለሬዲዮ ፖላንድ እንደተናገሩት፥ ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት የፊታችን እሁድ ይጀምራሉ።
አብረዋቸውም የፖላንድ ባለሀብቶች እንደሚጓዙም ነው የተናገሩት።
የጉብኝታቸው ዓላማ በኢትዮጵያ ያለውን የቢዝነስ አማራጭ ከመመልከት በተጨማሪም አገሪቱ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና ለመመረጥ ለምታደርገው ጥረት ድጋፍ ማሰባሰበም ነው ብለዋል።
ፖላንድ በአውሮፓውያኑ ከ2018 አስከ 2019 ምክር ቤቱን በተለዋጭ አባልነት የሚመሩ አገራትን ለመምረጥ በሚደረገው ምርጫ ለመሳተፍ አቅዳለች።
ፕሬዚዳንቱ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናትም ጋር ተገናኝተው ድጋፍ እንደሚጠይቁ ነው ሬዲዮው የዘገበው።