Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ጂቡቲ በአፍሪካ ግዙፍ ዘመናዊ ወደብ በመገንባት ለአገልግሎት ክፍት አደረገች

0 1,736

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ጂቡቲ በ590 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ያስገነባችው ዘመናዊ የዱራህሌ ወደብ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በ960 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ዶራሌ ሁለገብ ወደብ ለተለያዩ አገልግሎቶች ይውላል ተብሏል።

ወደቡ  590 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የፈጀ ሲሆን ወጪው በጂቡቲ ወደብ እና በቻይና መርቻንትስ ሆልዲንግስ በተባለ ተቋም ተሸፍኗል᎓᎓

የኢትዮያን 95 ከመቶ የሚሆነው የወጪ እና የገቢ ንግድ የሚተላለፈው በጂቡቲ ነው᎓᎓ ከዚህ በተጨማሪም ለብዙ የውጭ አገሮችና ለተለያዩ ተቋማት ወታደራዊ ይዞታ ሁና እያገለገለች ነው᎓᎓

ጂቡቲ አዲሱ በምትገነባው ዶራሌ ሁለገብ ወደብ ወደብ አልባዋ ደቡበ ሱዳን ከጦርነት ወጥታ ሰላም በሆነችበት ጊዜ እንደምትጠቀምበትም ተስፋ አድርጋለች᎓᎓

ወደቡ በዓመት እስከ ሰላሳ ሽህ የሚሆኑ መርከቦችን ያስተናግዳል ተብሏል።

ምንጭ:-ዥንዋ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy