Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ፌዴራላዊ ሥርዓቱ ድህነትን እየቀረፈ ነው!

0 334

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ፌዴራላዊ ሥርዓቱ ድህነትን እየቀረፈ ነው!

                                                       ቶሎሳ ኡርጌሳ

በመነሳት የሀገራችን ህዝቦችና መንግስት መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ጋር ለመቀላቀል የሰነቁትን ሩቅ አዳሪ ትልም ዕውን ለማድረግ በቅድሚያ ውስጣዊ ሰላማቸውን፣ ለጥቆም ከባቢያዊ ሰላምን ማረጋገጥ እንዳለባቸው በጥብቅ ያምናሉ። ‘ለውስጣዊ ሰላም መታጣት ያጋልጠናል’ ብለው ያመኑትን ድህነት ለመዋጋት ዘመቻ ከፍተዋል። የጎረቤቶች ሰላም እጦት በሀገራቸው ላይ የራሱን አሉታዊ አሻራ በማኖር በሩቅ ዓላሚነታቸው ላይ እንቅፋት እንደሚፈጥር ስለሚገነዘቡም፤ የጎረቤቶቻቸውን ሰላም በማገዝና በመደገፍ በሙሉ ቁርጠኝነት ተባብረው እየሰሩ ይገኛሉ።

በተለይም ለሰላም መታጣት ምክንያት በሚሆነው ድህነት ላይ ግልፅ የሆነ ሀገራዊ ትግል በመክፈት እያንዳንዱ ዜጋ ከመሚመዘገበው ዕድገት በየደረጃው ተጠቃሚ እንዲሆን በማድረግ ለችግሮች ተጋላጭነታችንን እጅግ ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ እየተቀነሰ ነው።  

በአሁኑ ወቅት መንግስትና ህዝብ ባካሄዱት ከፍተኛ ጥረት ሀገራችን በአለም አቀፍ ደረጃ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍ በቅታለች፡፡ በዚህም ከሰሃራ በታች ግዙፍ ኢኮኖሚ ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት በአምስተኛ ደረጃ፣ የነዳጅ ምርት ከሌላቸው ሀገሮች ደግሞ ቀዳሚውን ስፍራ የያዘችው ኢትዮጵያ የበርካታ ኢንቬስተሮችን ቀልብ በመሳብ ላይ ትገኛለች፡፡ ለዚህ ደግሞ የኢፌዴሪ መንግስት በሀገራችን የተፋጠነ ልማት ለማምጣት የሚያስችል ትክክለኛ ፖሊሲና ስትራቴጂ ከመንደፉም ባሻገር፤ በተግባር መተርጎም መቻሉ እንደሆነ ከማንም ከማንም የሚሰወር ጉዳይ አይመስለኝም፡፡

በርግጥ በሀገራችን እየተመዘገበ ለሚገኘው ለውጥ በዋናነት ሊጠቀስ የሚችለው ጉዳይ የጠራ መስመር የያዘ፣ ሀገራዊውን ወቅታዊና ተጨባጭ ሁኔታ በማገናዘብ በተግባር ላይ የሚያውል አመራርና በህዝባዊ ተሳትፎ የተደገፈ አቅጣጫን የሚከተል የልማታዊ መንግስት አካሄድ የመኖሩ ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ታዲያ የኢፌዴሪ መንግስት ሀገሪቱንና ህዝቦቿን ከድህነት ኋላቀርነት ለማላቀቅ የነደፈው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመር ተግባራዊ በማድረግ ተስፋ ሰጪ ዕድገት በማስመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም ባለፉት 26 ዓመታት በፌዴራላዊ ስርዓቱ ድህነትን መቅረፍ ችሏል።  

የኢፌዴሪ መንግስት የሀገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመቅረፅ የፀረ ድህነት ትግሉን ያቀጣጠለው መንግስታችን ህዝቡን በየደረጃው ተጠቃሚ የሚያደርግ ፈጣንና ተከታታይ ልማት በማስመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን መንግስት የበለጸጉት  ሀገሮች  ለመልማት  ባደረጉት  እንቅስቃሴ  በዓለማችን  ሥነ ምህዳር  ላይ በፈጠሩት  ቀውስ  ሳቢያ  በሚፈጠረው የአየር ንብረት መዛባት የተለያዩ አህጉሮች  በድርቅ  አደጋ ይጠቃሉ፡፡  ከእነዚህም ውስጥ  እንደ አፍሪካ  ያሉ ያላደጉ አህጉሮች ባልፈጠሩት ችግር ግንባር ቀደም ሰለባ ይሆናሉ፡፡  በተለይም  የምስራቅ አፍሪካ  ሀገሮች  የችግሩ  ተጠቂዎች  ከሆኑ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

በዚህ የበለጸጉት ሀገሮች  በፈጠሩት የአየር መዛባት  ምክንያት  በድርቅ  የምትጠቃው  ሀገራችን፤ ከድህነት ገና ሙሉ ለሙሉ ያልተላቀቀች  በመሆና የአየር ንብረቱ  የተለየ ክስተት  ሲያሳይ  በአንዳንዱ ዝናብ  አጠር  አካባቢዎች የምግብ  እጥረት  መከሰቱ የግድ ነው፡፡

ምንም  እንኳን  ድርቅና  ረሃብ  በአመዛኙ  በተፈጥሮ  የአየር  መዛባት  ምክንያት  የሚፈጠሩ  ቢሆኑም፤ ድርቅ በዝናብ  እጥረት   ሳቢያ  የሚፈጠርና  ጊዜያዊ  የምርትና  ምርታማነት  መስተጓጎልን  ሊያስከትል  የሚችል  ችግር ነው፡፡  ረሃብ ግን በተከታታይ  በሚፈጠር ድርቅ ሳቢያ በሚከሰት  የምግብ  እጥረት  ህብረተሰቡ  የሚላስና  የሚቀመስ  ሳይኖረው  በመቅረቱ  ለሞት  የሚያበቃ  ችግር  መሆኑ  ይታወቃል፡፡ ርግጥ ከሀገራችን ተጨባጭ  ሁኔታ  አኳያ  ድርቅ  እንጂ፤  ረሃብ  አለመኖሩ  ከዚህ አንፃር ከሚያቀነቅኑ ወገኖች የተሰወረ ጉዳይ  አይመስለኝም፡፡ ይሁንና ጉዳዩን የፖለቲካ ማራገቢያ  ለማድረግ  ሲሉ ድርቁን ሆን ብለው ወደ “ረሃብነት” ሲቀይሩት ተስተውሏል፡፡

ዳሩ ግን እውነታው ይህ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ወቅቶች የሚከሰተው ድርቅ የተፈጠረው ድርቅ እንጂ ረሃብ አይደለም፡፡ በሀገሪቱ በረሃብ ሳቢያ የሞተም ሆነ የሚሞት አንድም ሰው የለም፡፡ ምክንያቱም መንግስት ረሃብ እንዳይከሰት ከፍተኛ ስራዎችን በማከናወኑ ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት  የመንግስት ትኩረት ምንም ዓይነት የአየር ንብረት መዛባትና ድርቅ ቢያጋጥምም፤ ህዝባችን የማይራብበት ሁኔታን በመፍጠር ላይ ሲረባረብ ቆይቷል፡፡ እኔ እስከሚገባኝ ድረስ መንግስት ከአጭር ጊዜ አኳያ በተፈጥሮ ችግር ምክንያት የሚከሰተውን ድርቅ ለመከላከል በፍጥነት በመድረስና ዕርዳታ ማድረግ  እንዲሁም ድጋፉ ልማታዊ  በሆነ አኳሃን  ጥቅም ላይ  እንዲውል አድርጓል፡፡ እያረረገም ነው፡፡

በተደረገው ድህነትን የመቅረፍ ጥረት በዚህም ምክንያት ድርቁ ወደ ረሃብነት እንዳይሸጋገር የሚያደርጉ ተግባራትን  አከናውኗል፡፡ ይህም  አንድም  ሰው እንዳይሞት ያበረከተው አስተዋጽኦ  ከፍተኛ  ከመሆኑም  በላይ፤  መንግስት  ለዜጎቹ  ያለውን ከፍተኛ  የኃላፊነት ስሜት  የሚያመላክት ነው፡፡ ለነገሩ እንኳንስ አሁን  ተአምር ሰሪነቱ  በተግባር በመረጋገጥ ላይ የሚገኘው የልማት ስትራቴጂ  ከፍተኛ ዕድገት እየተመዘገበና በድርቅ ነባራዊ ማዕቀፍ  ውስጥ ሆነን ረሃብ  እንዳይፈጠር በተቻለበት በአሁኑ ጊዜ ቀርቶ፤  ቀደም ባለው ጊዜም በርካታ ሚሊዮን ህዝብ ለምግብ እጥረት በተዳረገበት ወቅትም ቢሆን ወደ ረሃብ ደረጃ አልገባንም፡፡ ልንገባም አንችልም፡፡  

እናም መንግስት በአየር ንብረት መዛባት ምክንያት የተፈጠረን ነባራዊ ሁኔታን  ለመቋቋም በዝናብ አጠር አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦች ድርቁን እንዲቋቋሙ ስትራቴጂውን  ተመርኩዞ  ዜጎችን ውኃ  ወደ አለበት ቦታ የማጓጓዝ  ዓይነት  መጠነ- ሰፊ  ተግባራትን  በማከናወኑ ያኔም ቢሆን ረሃብ  ሊከሰት አለመቻሉን  መገንዘብ  ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሁኔታ የተፈጠረው ፌዴራላዊ ሥርዓቱ በፈጠረው ምቹ ሁኔታ ነው፡፡  

ከዚህ በተጨማሪ የፌዴራል ሥርዓቱ በፈጠረው ምቹ ሁኔታ ዛሬም ሀገራችን ከድህነት ለመውጣት ባደረገችው ጥረት ውጤታማ እየሆነች ነው፡፡ በተለይም የሀገራችንን ህዝቦች አንገት ሲያስደፋ የነበረውን ድህነት ባለፉት 26 ዓመታት ውስጥ በግማሽ ለመቀነስ እንደተቻለ መረጃዎች ያመለክታሉ። በዚሀም የድህነት መጠኑ በ1983 ዓ.ም ከነበረበት 48 በመቶ አካባቢ አሁን ላይ ወደ 23 ነጥብ 4 በመቶ ወርዷል፡፡

መንግስት ከህዝቡ ጋር በመሆን ባከናወነው ከፍተኛ ጥረት በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አጠቃላይ ኢኮኖሚውን በ10 ነጥብ አንድ በመቶ ማሳደግ ተችሏል፡፡ በሀለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ሁለት ዓመት የሚጠጋ ጊዜም ቢሆን መልካም ጅምሮችን ማየት ችለናል፡፡ ለምሳሌ ያህልም በ2008/2009 ዓ.ም የመኸር ምርት ብቻ ከ320 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን መጥቀስ ይቻላል፡፡

ሀገራችን በፌዴራላዊ ሥርዓቱ ጥላ ስር በተመቻቸው የልማት ዕቅድ ድህነት የዚህች ሀገር መገለጫ የማይሆንበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ ማድረግ ይቻላል፡፡ እስካሁን ያለፍንባቸው የልማት መንገዶች የሚያረጋግጡት ይህንኑ ነው፡፡ በመሆኑም ፌዴራላዊ ሥርዓቱ የኢትዮጵያን ዋነኛ ችግር በመቅረፍ ላይ የሚገኝ በመሆኑ፣ ሥርዓቱን እንደ ዓይናችን ብሌን ልንጠብቀው ይገባል እላለሁ።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy