Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ፍርድ ቤቶችና የዴሞክራሲ ተቋማት የሚሰጡት ውሳኔ ተፈጻሚ ባለመሆኑ ፍትሕ ተዛብቶብናል – ቅሬታ አቅራቢዎች

0 419

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ፍርድ ቤቶችና የዴሞክራሲ ተቋማት የሚሰጡት ውሳኔ ተፈጻሚ ባለመሆኑ ፍትሕ እንደተዛባባቸው ቅሬታ አቅራቢዎች አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሰጥተዋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም የዴሞክራሲ ተቋማትን እና የፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ተግባራዊ ያላደረጉ ተቋማት መኖራቸውን ባደረገው ቅኝት አረጋግጧል።

ወይዘሮ የሺ ቸኮል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ነዋሪ ሲሆኑ፥ የቀበሌ ቤት ነበራቸው፤ ሆኖም ደባል ነዎት በሚል ከቤታቸው እንዲወጡ ይታዘዛሉ።

ግለሰቧ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደው ከከፍተኛ ፍርድ ቤት እስከ ሰበር ድረስ ተከራክረው ቤቱ እንደሚገባቸው ተወስኖላቸው፥ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ ጋር የባለቤትነት ውል ተዋውለዋል።

ይሁን እንጅ ከተወሰነ ሁለት ዓመት ያለፈው የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ተግባራዊ ባለመሆኑ የቤቱ ባለቤት መሆን አልቻሉም።

ወይዘሮ የሺ ላይ የታየው የፍትሕ አፈጻጸም መዘግየት በአንድ በኩል የዜጋዋን መብት ያላከበረ ሲሆን፥ በሌላ በኩል የፍትሕም ሆነ የዴሞክራሲ ተቋማት ውሳኔን ተግባራዊነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ነው።

የወይዘሮ የሺ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የዴሞክራሲ ተቋማት የሚወስኗቸው ውሳኔዎች ተፈጻሚ ሳይሆኑ ይታያሉ።

ከዚህ ቀደም በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አዳሚ ቱሉ ጸረ ተባይ መድሃኒት ፋብሪካን በሚመለከት ተከታታይ ዘገባዎች ተዘግበው ነበር።

ይህም ፋብሪካው የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን ምርቶች እያመረተ ስለመሆኑ በበርካታ ተቋማት መረጋገጡን የሚያሳይ ነው።

ይህንን ያጋለጡት በድርጅቱ ለረጅም ጊዜ ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ አምደማርያም መጬ ወንጀሉን በመጠቆማቸው ከስራቸው እንዲባረሩ አድርጓቸዋል።

ግለሰቡ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና ለህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ቢያመለክቱም፥ ተቋማቱ ችግሩ ስለመድረሱ እስከሚጣራ ግለሰቡ በስራቸው ላይ ይቆዩ ቢሉም ፋብሪካው ግን አሻፈረኝ ብሏል።

ፋብሪካው ጊዜ ያለፈበትን ምርት አምርቶ ሲሸጥ የሚመለከታቸው አመራሮች ተጠያቂ መሆን ቢኖርባቸውም፥ ተግባራዊ ባለመሆኑ አቶ አምደ ማርያምም ጉዳያቸው ምላሽ አለማግኘቱን ይናገራሉ።

የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቢ ህግ ጌታቸው አምባዬ፥ ፍርድ ቤቶች ገለልተኛ ተቋማት በመሆናቸው ውሳኔያቸው ሊከበር እንደሚገባ ገልፀው፥ ተቋማትም ሆነ ግለሰቦች በዚህ ጊዜ ይግባኝ ማለት እንጂ ውሳኔውን መጣስ የለባቸውም ብለዋል።

ያለተገባ የውሳኔ ጥሰት ሲፈፀምም ፍርድ ቤቶች እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ አለባቸው ነው ያሉት ጠቅላይ ዓቃቢ ህጉ አቶ ጌታቸው።

በሌላ በኩል እንደ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ያሉ የዴሞክራሲ ተቋማት ያሳለፉትን ትዕዛዝ መፈጸም የተቋማት ግዴታ ነው የሚሉት ጠቅላይ አቃቢ ህጉ፥ የዴሞክራሲ ተቋማቱም በዜጎች ላይ የሚያደርሱትን ጭቆና ለማስቆም ለተቋማት ትዕዛዝ ማስተላለፍ አለባቸው ይላሉ።

የፍርድ ቤቶች ውሳኔ እንዲከበር የአፈጻጸም ስርዓቱ ላይ ጠንካራ ክትትሎችን ማድረግ፥ የዴሞክራሲ ተቋማት ውሳኔያቸውን የመፈጸም አቅማቸው እንዲጠናከር ተገቢ ስራዎችን መስራት ይገባል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy