Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ለተጠያቂነት የአሰራር ስርአት

0 605

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ለተጠያቂነት የአሰራር ስርአት/ ስሜነህ/

የመንግሥት የስልጣን አካላት የሚባሉት  ሕግ አውጭው (ፓርላማው)፣ ሥራ አስፈጻሚው (የመንግሥትን ሥራ የሚያከናውነው) እና ሕግ ተርጓሚው (የዳኝነቱ አካል) እርስ በርስ እየተናበቡ መሥራት የሚችሉት የተጠያቂነት መርህ ተግባራዊ እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ሥርዓተ መንግሥቱ ጤናማ ሆኖ ሕዝብን ማገልገል የሚቻለው በሕጉ መሠረት አንዱ ለሌላው ተጠያቂነትን በተገቢው መንገድ እያሳየ፣ የተሰጠውን ኃላፊነት መወጣት ሲችል  ነው፡፡ ይህ የእርስ በርስ ቁጥጥር የሚደረግበት ሥርዓት ደግሞ ሕግ ያከብራል፣ ያስከብራል፣ ሕገወጥነትን ጠንክሮ ይፋለማል፣ የሕዝብ ጥያቄን በአግባቡ ይመልሳል፡፡ በሕገ መንግሥቱም ሆነ በተለያዩ ሕጎች የወጡ ድንጋጌዎችን መሠረት ያደረጉ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶችን ከመጠበቁም በላይ፣ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እንዲሰፍን ይሠራል፡፡ ተጠያቂነት ከሌለ  ግን ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት አይቻልም፡፡

የተጠያቂነት መርህ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠሪነታቸው በየደረጃው ለሚገኙ ምክር ቤቶች  የሆኑ ተቋማት  በአስፈጻሚው ተፅዕኖ ሥር ሊወድቁ አይገባም፡፡ ፓርላማውን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች ሥራ አስፈጻሚውን ይቆጣጠራሉ እንጂ፣ አስፈጻሚ በተቃራኒው የበላይ መሆን የለበትም፡፡ በሕግም የተከለከለ ነው፡፡ የሕግ ተርጓሚውም ቢሆን ከአስፈጻሚው አካል ጫና ሊደርስበት አይገባም፡፡ተጠያቂነት በመጥፋቱ ብቻ ግን ከላይ የተዘረዘሩት በሙሉ ተግባራዊ አልሆኑም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ይፋ በሚደረጉ ጥናቶች በተለይ ደግሞ የፖሊሲ ጥናት ማእከል ሰሞኑንም ይፋ ባደረገው ጥናት ጭምር የችግሩ ግዝፈት ታይቷል፡፡በተለይ በከተሞች ደግሞ ችግሩ እየተባባሰ እንጂ በጥልቅ ተሃድሶው እንኳን ሊገታ እንዳልቻለ ነዋሪዎች እየገለጹ ነው። በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለከተሞች የተደረጉ የህዝብ ውይይቶች ያረጋገጡትም ይህንኑ ነው።

የአራዳ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ተመራጮች በክፍለ ከተማው ከሚገኙ 10 ወረዳዎች የተውጣጡ ነዋሪዎች በተሳተፉበት የመራጭና ተመራጭ የጋራ የምክክር መድረክ ሰሞኑን አካሂደው ነበር። በዚህ መድረክ ታዲያ ነዋሪዎቹ ያነሷቸው ጉዳዮች ከላይ የተመለከተውን የተጠያቂነት መርህ ተግባራዊ አለመሆን  የሚጠቁሙ ናቸው። በወረዳዎችና ክፍለ ከተማው በሚከናወኑ ተግባራት ያለው አለመናበብ፣ የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት፣ የመሰረተ ልማቶች አለመሟላትና የመሰረታዊ ሸቀጦች ፍትሃዊ ስርጭት አለመኖር ከተነሱት ችግሮች ዋነኞቹ ሲሆኑ እነዚህም በቀጥታ ከተጠያቂነት መርህ ጋር የተያያዙ ናቸው።

የአስፈጻሚ አካላት የአቅም ውስንነትና ቁርጠኛ አለመሆን፣ የስብሰባዎች መብዛት፣ እንዲሁም የጸጥታ ችግር ምክር ቤቱ በበቂ ትኩረት አልሰራባቸውም ሲሉ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል። የክፍለ ከተማው የዘርፍ አስፈጻሚዎችና ኃላፊዎች ከነዋሪዎቹ የተነሱ አብዛኛዎቹ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ትክክለኛ መሆናቸውን አምነዋል። ይህ የሚያመላክተው ደግሞ የነዋሪዎች ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ የክፍለ ከተማው ምክር ቤት አስፈጻሚውን አካል የመከታተልና የመቆጣጠር ተግባርና ሃላፊነቱን እንዳልተወጣ ወይም ደግሞ በአስፈጻሚው ተጽእኖ ስር መውደቁን ነው።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተደረጉትም ውይይቶች በተመሳሳይ ይህንኑ የተጠያቂነት መርህ መጥፋት ያረጋገጡ ናቸው። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በክፍለ ከተማው ከሚገኙ የምክር ቤቱ አባላት፣ ከሁሉም ወረዳዎች የተወጣጡ የህብረተሰብ ተወካዮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር  ባካሄደው ውይይት ላይ የአስተዳደርና የአሰራር ስርአቶች ግልጽ አለመሆን፣ ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን በወቅቱና በአግባቡ አለመመለስ በየወረዳው እና በክፍለ ከተማው ጎልተው የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ስለመሆናቸው ተገልጿል። በተጨማሪም ስራ አጥ ወጣቶችን የማደራጀት እና የጤና ጣቢያዎችን የማስፋፋት ስራ መዳከም፣ በአካባቢ የመሰረተ ልማትና በቂ የስፖርት ማዘውተሪያዎች አለመኖር ከመልካም አስተዳደር ችግሮች እጦት አኳያ የሚታዩ ክፍተቶች መሆናቸውንም ህዝቡ አስታውቋል።  

በየክፍለ ከተሞቹ  ከተደረጉት የውይይት መድረኮች  አንድ ክፍለከተማ እንጨምር። የልደታ ክፍለ ከተማ የሁሉም ወረዳዎች የህብረተሰብ ተወካዮች አገር አቀፍ የፍትህ ሳምንትን አስመልክቶ ውይይት አካሂደዋል።

በዚህ ወቅት ተወካዮቹ እንዳሉት የፍትህ ስርዓቱ ላይ አሁንም የሕዝብ ቅሬታ በመኖሩ ለችግሩ መፍትሔ ለማምጣት ተጨማሪ ጥረት መደረግ እንደሚኖርበትና በፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለሚነሱ ቅሬታዎች በአግባቡ መፍትሄ በመስጠት የፍትህ አካላት የሚያደርጉት አስተዋጽኦም አነስተኛ እንደሆነ ተወካዮቹ ጠቁመዋል።

በፍትህ ተቋማት ላይ በቅንጅት አለመሥራትና ሕብረተሰቡ በፍትህ ጉዳይ ላይ ለሚጠይቀው አገልግሎት ፈጣን ምላሽ አለማግኘት ከሚታዩ ችግሮች መካከል ተጠቃሽ እንደሆኑ ተወካዮቹ ገልጸዋል።ለክስ የሚያስፈልገውን መረጃ ለማሰባሰብ ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ የጠቆሙት ተወካዮቹ፤ ማስረጃ የቀረበባቸውን ተጠርጣሪዎች ፈጥኖ ለፍርድ የማቅረብ ችግር እንደሚታይም ተናግረዋል። እንደ ተወካዮቹ ገለጻ በወንጀል ፍትህ አስተዳደር፣ ከአቤቱታ ምርመራ ጀምሮ እስከ ውሳኔ ማስፈጸም ባሉ ሂደቶች ላይ በፍትህ አካላት መካከል የመናበብና ተቀራርቦ የመሥራት ክፍተቶችም አሉ። ይህ ደግሞ የተጠያቂነት መጥፋት ወይም ህግ ተርጓሚ የሚባለው አካል እንደምክር ቤቶቹ በተመሳሳይ በአስፈጻሚው ተጽእኖ ስር ስለመውደቁ ሁነኛ ማሳያ ነው።  

ሌላው ቀርቶ ‹ጥልቅ ተሃድሶ› በሚካሄድበት በዚህ ወቅት ጉቦ መቀበልም ሆነ በየደረጃው ሙስና መፈጸም ተጣጡፎ ቀጥሏል፡፡ አገልግሎት በሚሰጡ መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ በተሰገሰጉ ጉዳይ አስፈጻሚዎች አማካይነት በአደባባይ የሚፈጸመው ሌብነት የተጠያቂነት ያለህ እያለ ነው፡፡ በየደረጃው ካሉ አመራሮች ጀምሮ ፈጻሚዎች ድረስ የሚጠየቀው መማለጃ በሕግ የተፈቀደ ይመስላል፡፡ ቅሬታ ሲቀርብ የሚሰማ የለም፡፡ ይልቁንም ለሙስና የሚያበረታቱ ምክሮች ይለገሳሉ፡፡ ሕዝብ ደግሞ ‹መታደስ ማለት እንዲህ ነው ወይ?› እያለ ይጠይቃል፡፡ ተጠያቂነት በመጥፋቱ ብቻ ብዙ ነገሮች ከመስመራቸው እየወጡ ነው፡፡

ስለሆነም የህዝብ ምክር ቤቶችን ጨምሮ ሁሉም  የዴሞክራሲ ተቋማት የህግ የበላይነት እንዲከበር እና የተጠያቂነት አሰራር እንዲሰፍን  የተጣለባቸውን  ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ።የትም መሄድ ሳያስፈልጋቸው ከኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮምሽን ልምድ ሊወስዱ ይገባል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን  በኦሮሚያ ፣  አማራና ደቡብ  ክልሎች  አንዳንድ  አካባቢዎች  የተከሰተውን  ሁከት  አስመልክቶ ያደረገውን  የምርምራ  ውጤትና  ምክረ  ሀሳብ  ለህዝብ  ተወካዮች ምክር  ቤት  ማቅረቡና ምክር  ቤቱም  የምርመራ  ውጤቱንና  ምክረ  ሀሳቡን  በመርመር  ሪፖርቱን  መቀበሉና  ውሳኔዎች  ማሳለፉ  የዴሞክራሲያዊ  ተቋማቱ  ለህግ የበላይነት  መረጋገጥና  ለዜጎች  መብት  መከበር ይልቁንም ለተጠያቂነት መርህ መስፈን ያላቸውን ፋይዳ ያመላክታል ።

ስሜነህ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy