Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

መረጃ የሚሰጡ ግለሰቦች የሕግ ከላላ ሊደረግላቸው ነው

0 532

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መረጃ ለሚሰጡ ግለሰቦች የሕግ ከለላ የሚሰጥ ደንብ ሥራ ላይ ሊያውል ነው።

ሕጋዊ ከለላ የሚደረግላቸው ለህዝብ ጥቅም ሲባል ትክክለኛ መረጃን ለሚያቀብሉ ወይም ይፋ ለሚያደርጉ ሠራተኞች ነው ተብሏል።

የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነጻነት ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 590/2000 የማስፈጸም ሕጋዊ ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

የመረጃ ነፃነት ሕግን ለመተግበር የሚያግዙ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት ደግሞ ተቋሙ በሕግ ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል።

በዚህም መሰረት ‘መረጃ ለሚሰጡ ግለሰቦች’ የሕግ ከላላ የሚሰጥ ደንብ ማዘጋጀቱን ነው የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ልዑል ስዩም የተናገሩት።

ይህም በመሥሪያ ቤቶች አካባቢ የሚስተዋሉትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች መረጃዎች በግልጽነት በማስተላለፍ ለመታገል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ሠራተኞች መረጃን በማቀበላቸው እንዳይሸማቀቁና ከሥራ ገበታቸው እንዳይፈናቀሉ ለማስቻል ሕጋዊ ከላላ ለመስጠት መሆኑን አስረድተዋል።

በመሆኑም ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ ሠራተኞች መረጃ በማቀበል እንዲጋፈጡ ለማስቻል ሕጋዊ ከለላ እንዲኖራቸው ደንቡ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ደንቡ ከወር በፊት የሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዳጸደቀውና በቅርቡም በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ወጥቶ ወደ ሥራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ይህም መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥና የመረጃ ነጻነት አዋጁን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እንደሚያግዝ ነው የገለጹት።

በአዋጁ እንደተደነገገው ማንኛውም ሰው ከማንኛውም መንግሥታዊ አካል መረጃን የመጠየቅ፣ የማግኘት እንዲሁም የማስተላለፍ መብት አለው፡፡

ይህም የመንግሥትን አሠራር ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ውጤታማነቱን በማረጋገጥ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ያለመ ነው።

ይሁን አንጂ አሁንም ከመረጃና ከአሰራር ጋር በተያያዘ በአንዳንድ መሥሪያ ቤቶች  አሁንም ችግር እንደሚስተዋል ተናግረዋል።

በባለሙያዎች የአቅም ክፍተትና መረጃን በቴክኖሎጂ በመታገዝ የመሰደር፣ የመጠበቅና ፈጥኖ በመላክ ረገድ የሚስተዋሉ ክፍተቶች ናቸው ብለዋል።

እነዚህን ለማሻሻል ተቋሙ ተከታታይ ሥልጠናና ክትትል በማድረግ ሙያዊ እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በተጓዳኝ መረጃ በተከታታይ የማይሰጡ ተቋማትን በመለየት ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy