NEWS

በትግራይ ክልል ለወጣቶች ፈንድ ከቀረቡ 43 ሺህ ቢዝነስ ፕላኖች መካከል 2 ብቻ ተግባራዊ መሆናቸው ተገለጸ

By Admin

May 06, 2017

በትግራይ ክልል ለወጣቶች ፈንድ ተብሎ በተዘጋጀው መርሐግብር ከቀረቡት 43 ሺ ቢዝነስ ፕላኖች መካከል 2 ብቻ ወደ ተግባር መሸጋገራቸው ተገለጸ።

ቢዝነስ ፕላን ያቀረቡ ወጣቶች ለፋና ብሮድካስቲነግ ኮርፐሬት እንደተናገሩት ፥ቢዝነስ እቅዶቻቸውን ለሚመለከተው አካል ቢያቀርቡም በአፋጣኝ ወደ ተግባር ለመሸጋገር በአገልግሎት አሰጣጥ ችግር እየደረሰባቸው መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይ ለስራ አጥ ወጣቶች የሚጠየቁት የብድሩን 10 በመቶ ቁጠባ በጣም እንደከበዳቸውም ነው የተናገሩት፡፡

የትግራይ ክልል ጥቃቅንና ኣነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የከተሞች ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ሃይላይ አረጋዊ በበኩላቸው ፥በትግራይ የስራ አጥ ወጣቶችን ችግር ለመፍታት ስልጠናዎች እንደተሰጠ እና እንዲደራጁ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

እስከ አሁን በትግራይ ክልል ለወጣቶች ፈንድ ተብሎ በተዘጋጀው መርሐግብር ከቀረቡት 43ሺ ቢዝነስ እቅዶች መካከል 2 ብቻ ወደ ተግባር እንደተሸጋገሩ ነው የተናገሩት::

የኤጀንሲው ኃላፊ አቶ ሃይላይ እንዳሉት ፥10 በመቶ መቆጠብ የማይችሉ ስራ አጥ ወጣቶች ሳይቆጥቡ እስከ 30 ሺ ብር ብድር የሚያገኙበት ስርአት ተዘርግቷል።

ወጣቶቹ ወደ ስራ ያልገቡበትን  ምክንያቶች እና ችግሮች በመለየት  በግንቦት ወር 70 በመቶ ስራዎችን  ለመፈፀም መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል፡፡