Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በደብረ ብርሃን ከተማ ሁለት ህጻናት ተጣብቀው ተወለዱ

0 1,377

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ ሁለት ህጻናት ተጣብቀው ተወለዱ።

ትናንት በደብረ ብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል የተወለዱት ህጻናት በደረታቸው ነው የተጣበቁት።

ሁለቱም በጾታ ወንዶች ሲሆኑ ሶስት ኪሎ ግራም እንደሚመዝኑ፥ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተርና የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ፍስሃ ታደሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል።

የህጻናቱ ወላጅ እናትና ህጻናቱ በአሁኑ ሰዓት በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉም ነው ያሉት ዶክተር ፍስሃ።

ህጻናቱን የተገላገሉት ወላጅ እናት ከዚህ በፊት ወንድ ልጅ በሰላም መገላገላቸውን ጠቅሰው፥ በእርግዝና ወቅት የቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ስለ ሁኔታው ማብራሪያ የሰጡት ዶክተር ፍስሃ በበኩላቸው፥ ይህ አይነቱ አጋጣሚ በሆስፒታሉ ታሪክ የመጀመሪያው መሆኑን ነው የተናገሩት።

ሁኔታው ከመንታ አፈጣጠር ጋር የተያያዘ ነው ያሉት ዶክተር ፍስሃ፥ መንታ በሁለት አጋጣሚዎች ይፈጠራል ብለዋል።

የመጀመሪያው ከሁለት የወንድ የዘር ፍሬና ከሁለት የሴት የዘር ፍሬ ወይም እንቁላል ሲፈጠር፥ ሁለተኛው ደግሞ ከአንድ የወንድ የዘር ፍሬ እና ከአንድ እንቁላል እንደሚፈጠር አስረድተዋል።

ይህ የመንታነት ሂደት በቀናት ውስጥ ወደ ሁለት የሚከፈል ሲሆን፥ የክፍፍል ስርዓቱ ከሶስተኛው ቀን ጀምሮ እስከ 13ኛው ቀን ድረስ ከሆነ በጾታም ሆነ በባህሪ ሊለያዩ የሚችሉ ሁለት ልጆች እንደሚወለዱ አንስተዋል።

ከዚህ በተቃራኒው ከሆነና የክፍፍል ስርዓቱ በተባለው ጊዜ ሳይሳካ ቀርቶ ከዚያ በኋላ ባሉት ሁለት ቀናት የሚከሰት ከሆነ ደግሞ፥ ሁለቱ ልጆች ተጣብቀው ሊወለዱ የሚችሉበት ሁኔታ እንደሚፈጠርም ነው ያስረዱት።

አሁን ላይ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ያሉት ህጻናት፥ ከደረታቸው በተጨማሪ ልብ እና ሳንባ ተጋርተው ሊሆን ስለሚችልም ለተጨማሪ ህክምና ወደ አዲስ አበባ ይላካሉ ተብሏል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy