Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በድርጅታቸው ስም ከ3 ሚሊየን ዶላር በላይ ከንግድ ባንክ በመበደር ገንዘቡን ወደ ዱባይ ያሸሹት ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ

0 1,197

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ባቋቋሙት ኩባንያ ስም 3 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመበደርና ገንዘቡን ወደ ዱባይ በማሸሽ የተከሰሱት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።

ተከሳሾቹ በትውልድ ደቡብ አፍሪካዊ በዜግነት ደግሞ አሜሪካዊው ማይክል ማሰን እና ትውልደ ግብጻዊውና በዜግነት አሜሪካዊ የሆኑት ሚስተር አይመን አብዱል ሞትሊን ናቸው።

የጠቅላይ አቃቢ ህግ ክስ እንደሚያመላክተው ተከሳሾች ከ2003 እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው ስታር ፓይፕ በተባለ ሃገር በቀል ኩባንያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተለያዩ ማሽነሪዎች ማስመጫ በሚል ገንዘብ ተበድረዋል።

ተከሳሾቹ የተበደሩትን 3 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወደ ዱባይ በማሸሽና በራሳቸው የሂሳብ አካውንት በማስገባት ሃሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት አገልግሎት የማይሰጡ በርካታ ማሽነሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ ማስገባታቸውም በክሱ ተጠቅሷል።

በአጠቃላይ ተከሳሾቹ በከባድ የማታለል፣ በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሃሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ወንጀሎች ተከሰዋል።

ተከሳሾች ወንጀሉን አለመፈጸማቸውን በማስረዳት ክደው ተከራክረዋል።

ከሳሽ አቃቢ ህግ በበኩሉ የሰነድ እና የሰው ምስክር አቅርቦ ለችሎቱ አሰምቷል።

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎትም፥ 2ኛ ተከሳሽ ሚስተር አይመን አብዱል ሞትሊን በ25 አመት ፅኑ እስራትና በ252 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።

ከዚህ ባለፈም 1ኛ ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርቡ በማዘዝ ለግንቦት 25 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

 

 
በታሪክ አዱኛ

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy